ዲጂታል የኢንሹራንስ እና የአረቦን ብድር አገልግሎት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከኒያላ ኢንሹራንስ እና ከካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ጋር በመተባበር ዲጂታል የኢንሹራንስ እና የአረቦን ብድር አገልግሎትን ሀምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ አስጀምሯል፡፡

በመርሃ ግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዲጂታል ባንኪንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ መቅደስ በቀለ፣ የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ቺፍ ከስተመር ማኔጅመንት ኦፊሰር አቶ ተገኝ ማስረሻ፣ የካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሀም ጥላሁን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የተለመደው የኢንሹራንስ አገልግሎት ደንበኞች ቅርንጫፍ ቢሮ ድረስ በአካል ሄደው የሚያገኙት የነበረ ሲሆን ዲጂታል የኢንሹራንስ እና የአረቦን ብድር አገልግሎት በማንኛውም ሰአት እና ቦታ ሆነው ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም የኢንሹራንስ ሽፋን ማግኘት መቻላቸው ጊዜን ከመቆጠብ አልፎ በሀገራችን የሚታየውን የኢንሹራስ ተደራሽነት ችግር በሰፊው ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በስምምነቱ መሰረት የኒያላ ኢንሹራንስ ደንበኞች ወደ ኢንሹራንስ ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ቦታ ሆነው ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ለንብረታቸው የመድን ሽፋን ዋስትና መግዛት የሚችሉበት ሙሉ በሙሉ ዲጂታል የሆነ አገልግሎት ሲያስጀምር፤ ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ የቴክኖሎጂ እና የዲጂታል መተግበሪያ የማቅረብ ድርሻ ሲኖረው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የአረቦን ክፍያቸውን ተበድረው መክፈል ለሚፈልጉ ደንበኞች የብድሩን ገንዘብ አቅርቦት ተደራሽ ያደርጋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከሉሲ ኢንሹራንስ ጋር ተመሳሳይ አገልግሎት ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ከባለአክሲዮኖች ጋር የሚደረገው የውይይት መድረክ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከባለአክሲዮኖቹ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችለውን የውይይት መድረክ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም...

ባንኩ የተቋቋመበትን ዓላማ እንዲያሳካ ያልተቆጠበ ድጋፍ እናደርጋለን – ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ባንኩ የተጣለበትን ሀገራዊ እና ማህበራዊ ኃላፊነት በተሟላ ሁኔታ ተወጥቶ የተቋቋመበትን ዓላማ እውን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በእንጦጦ ተራራ...