
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “በሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎት አሰጣጥ” ዙሪያ ለስድስት ተከታታይ ወራት ያሰለጠናቸውን ሠራተኞች ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል አስመርቋል፡፡
በምረቃ ስነ- ስርዓቱ ላይ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቺፍ ፋይናንስ እና ሰፖርት ኦፊሰር አቶ ዳሳ ጎቤ፣ ቺፍ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ኦፊሰር አቶ ሲሳይ አየለ እንዲሁም የባንኩ የማኔጅመንት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
ስልጠናው በአጠቃላይ የባንክ አገልግሎት እንዲሁም በአዳዲስ የባንክ አዋጆች እና መመሪያዎች ዙሪያ ትኩረት ተደርጎ መሰጠቱን የባንኩ የፋይናንስ እና ሰፖርት ቺፍ ኦፊሰር አቶ ዳሳ ጎቤ በመርሃ ግብሩ ወቅት ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል።



የላቀ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ዘመኑን የዋጀ ሠራተኛ ሊኖር እንደሚገባ በእንኳን ደስ አላችሁ ንግግራቸው የገለፁት የባንኩ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ማሞ ይኸን እውን ለማድረግ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎት ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎችን ለሰራተኞቹ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
በምርቃት መርሃ ግብሩ የባንኩን ብራንድ አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ በበኩላቸው “ማንኛውም ሰው የራሱ የሆነ መዳረሻ ይኖረዋል” ለመዳረሻው ደግሞ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ብርቱ አጋር ነው” ብለዋል።
የዛሬ ተመራቂዎች የባንኩ አምሳደሮች መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ቢኒያም ስልጠናውን በስራቸው ተግባራዊ በማድረግ የባንካችንን ዓላማ ማሳካት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
ስልጠናው በእውቀት፣ በክህሎት እና በአመለካከት ላይ ትኩረት ተደርጎ መሠጠቱ ይበልጥ ብቁ እንዲሆኑ እንደሚያስችላቸው የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
የካፒታል የፋይናንስ ልህቀት ማዕከል አክሲዮን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ጌታሁን ናና በበኩላቸው ባንኩ ሰው ላይ እየሰራ መሆኑን አውስተው፤ ተተኪ የባንክ ባለሙያዎችንና አመራሮችን ለማፍራት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።
ስልጠናውን ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከካፒታል የፋይናንስ ልህቀት ማዕከል አክሲዮን ማህበር ጋር በመተባበር ከ70 በላይ ሠራተኞች የተሰጠ ሲሆን 35 የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እንዲሁም ከ35 በላይ አካውንታት ናቸው።
ስልጠናው ላለፉት ስድስት ወራት በሳምንት ለሁለት ቀን የተሰጠ ሲሆን ባለፈው ዓመትም ተመሳሳይ ስልጠና የወሰዱ ከ28 በላይ ሰራተኞችን አሰልጥኖ ማስመረቁ ይታወቃል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!