
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል እያካሄደ ያለውን የባንኩን ከፍተኛ ደንበኞች የመጎብኘት እና የውይይት መርሃ ግብር አጠናክሮ ቀጥሏል።
የጉብኝት መርሃ ግብሩ ታኅሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአርፋሳ ጠቅላላ ንግድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ተከናውኗል።
በጉብኝት መርሃ ግብሩ የባንካችን የቦርድ አባላት እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአርፋሳ ጠቅላላ ንግድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ጋር በርካታ ዓመታትን አብረው ሲሰሩ መቆየታቸውን በውይይቱ ወቅት የገለፁት የባንኩ ኃላፊዎች በቀጣይም ለጋራ ስኬት በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የባንኩን ከፍተኛ ደንበኞች እና ባለድርሻ አካላት ለጋራ ዕድገት በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት ማድረግ እና አዳዲስ የቦርድ አባላትን ከደንበኞች ጋር ማስተዋወቅ የመርሃ ግብሩ ዓላማ መሆኑን የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ ጌታቸው ገልፀዋል።



የባንኩ ቦርዶች እና ኃላፊዎች የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ ለመጎብኘት በመምጣታቸው ምስጋናቸውን ያቀረቡት የድርጅቱ ኃላፊዎች በቀጣይም ከግሎባል ባንክ ጋር በጋራ ለመስራት እንደተለመደው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
አርፋሳ ጠቅላላ ንግድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ በመሰማራት ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የገለፁት የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ ደገፋ ስሜ ለድርጅቱ ስኬታማነት የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ድጋፍ አይነተኛ ሚና መጫወቱን ገልፀዋል።
የባንኩ ደንበኞች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ መልኩ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ያወሱት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ፤ በቀጣይም ያልተቆጠበ ድጋፍ ለማድረግ ባንኩ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል የደንበኞችን የስራ እንቅስቃሴ የመጎብኘት መርሃ ግብር በተለያዩ ድርጅቶች የተከናወነ ሲሆን ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!