Search
Close this search box.

ግሎባል ባንክ አ.ማ. ስራ አመራር የተሰጠ መግለጫ

Share the Post:

የተከበራችሁ የ ግሎባል ባንክ ደንበኞች፣ ባለአክሲዮኖችና ሰራተኞች ባንካችን ባለፉት ዓመታት በበርካታ የባንክ የስራ ዘርፍ አመርቂ የሚባል ውጤት እያመጣ ከተፎካካሪ ባንኮች አንጻር ፈጣን እድገት እያስመዘገበ የሚገኝ ባንክ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

ባንኩ ባለፉት አምስት ዓመታት (እስከ ሜይ 31፣ 2021) ውስጥ በበርካታ መመዘኛዎች ከፍተኛ የሚባል እድገት ያሳየ ሲሆን በጠቅላላ ሃብት በ58.5%፣ በትርፍ በ94% እንዲሁም በተከፈለ ካፒታል በ40% አማካይ እድገት አስመዝግቧል፡፡ ከነዚህም በተጨማሪ ደቡብ ግሎባል ባንክ በተቀማጭ ገንዘብ፣ በብድር አሰጣጥ፣ በገቢና በሌሎችም መስፈርቶች ከፍተኛ የሚባል እድገት በማስመዝገብ በባንክ ኢደስትሪው ውስጥ ያለውን ደረጃ እያሻሻለ በከፍታ እየገሰገሰ የሚገኝ ባንክ ነው፡፡

ዛሬ ላይ ባንኩ ከብር 1.3 ቢሊዮን በላይ የተከፈለ ካፒታል ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን የተደራሽነት አድማሱን በማስፋትም በክልሎችና በአዲስ አበባ 111 ቅርንጫፎችን በመክፈት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ አርኪ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ሰፊ የስራ ዕድልም በመፍጠር 1977 የሚሆኑ ዜጎችን በአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎቹ በማሰማራት ለሃገራችን የበኩሉን አስተዋፅዖ እያበረከተ ሲሆን በከፍተኛ ግብር ከፋይነቱም በአግባቡ ግዴታውን የሚወጣ ምስጉን ባንክ ነው፡፡

ባንኩ ባሳለፍነው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የብር 1 ቢሊዮን ገቢ እና የብር 10 ቢሊዮን በላይ የሃብት መጠንን ያስመዘገበ ሲሆን በዘንድሮ ዓመትም ከዚህ በተሻለ መልኩ እየሰራ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ይህ የባንኩ እድገትና መልካም አፈጻጸም ያላስደሰታቸው አንዳንድ ግለሰቦች በአሉታዊ መንገድ ጋዜጦችን እና በማህበራዊ ድህረ ገጾችን በመጠቀም የባንኩን መልካም ገፅታ ለማጠልሸት ብሎም እድገቱን ወደ ኋላ ለመመለስ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያደረጉ እንደሆን ተገንዝበናል፡፡

ይሁን እንጂ የተከበሩ ባለአክሲዮኖቻችንና ደንበኞቻችን የባንኩን እድገትና ደረጃ በእጅጉ እንደሚገነዘቡት የምናውቅ ሲሆን ገፅታን ለማበላሸት በሚደረጉ መሰል የማህበራዊ ሚዲያ ዜናዎችም ሳይደናገጡ ከባንኩ ጋር ያላችውን የስራ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር ከእኛ ጎን እንደሚቆሙ የእድገት ግስጋሴያችንንም በጋራ እንደምንቀጥል የባንኩ ስራ አመራር በጽኑ ያምናል፡፡

በውጭ ምንዛሬ አስተዳደር በኩልም ካለፉት አመታት ተንጠልጥለው የመጡ የተወሰኑ የዕዳ ጫናዎች ቢኖሩም አብዛኞቹን በመክፈል እያቃለለ ይገኛል፡፡ ከፋይናንስ መዝገብ ጋር በተገናኘ የቀረቡት ማስተካያዎች በውጭ ኦዲት በስርዓት ተገምግመውና ማሻሻያ ተደርጎባቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተላከ ሲሆን የባንኩን አዎንታዊ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህ ማስተካከያ ተደርጎበት የተሻሻለው የኦዲት ሪፖርትም ቢሆን የሚያሳየው የባንኩ ግርድፍ ትርፍ ከብር 243 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ ሲሆን ይህም አኃዝ ጥሩ አፈፃፀምን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በቀደመው ሂሳብ ሪፖርት ላይ የነበረው ልዩነት የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ዕዳ ላይ ሊታሰብ የሚገባው የምንዛሬ ልዩነት በግልፅ አልቀረበም የሚል ሲሆን ይህም ባንኩ ላለፉት አመታት ሲጠቀምበት የነበረው የምንዛሬ ልዩነት ተከፋይ (Realized ) በሆነ ወጪ የመያዝ አካሄድ ነበር ነገር ግን ተከፋይ ያልሆነ (unrealized) ወጪም በተጨማሪ መሰላት አለበት የሚል አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን ይህንን ተግባራዊ በማድረግ የፋይናንስ ሪፖርታችን ተስተካክሎ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡