Search
Close this search box.

ግሎባል ባንክ ‹ የቂርቆስ ፓርክን › ለማልማት 3000 ካሬ ቦታ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተረከበ ፡፡

Share the Post:

ባንካችን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቄራ አትክልት ተራ አካባቢ ለማህበረሰቡ ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥና የከተማዋን ገፅታ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀይር ፓርክን ለማልማት ከክፍለ ከተማው አስተዳደር ተረክቧል ፡፡
የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በርክክብ ስነስርአቱ ላይ እንደተናገሩት የሚገነባው ፓርክ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ገፅታ የሚያላብሳትና ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፓርክ ለመገንባት ባንኩ በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል ፡፡
የሚገነባው ፓርክ የከተማዋን ውበትና ፅዳት ከማስጠበቁም በላይ በአካባቢው ለሚገኙ እናቶች እና ወጣቶች የስራ እድልን ይፈጥራል ብለዋል ፡፡
የባንኩ ፕሬዝደንት ክቡር ዶክተር ተስፋዬ ቦሩ ደቡብ ግሎባል ባንክ በተሰራው የፓርክ ዲዛይን መሰረት የአዲስ አበባ ከተማን የሚመጥን ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ፓርክ በተቀመጠው የግዜ ገደብ ሰርተን ለማስረከብ ዝግጁ ነን ብለዋል ፡፡

በርክክብ ስነ – ስርአቱ ላይ የደቡብ ግሎባል ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ፤ የባንኩ ፕሬዝደንት እንዲሁም ከፍተኛ የባንኩ የማኔጅመንት አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ፡