ግሎባል ባንክ የተሰራው  ቂርቆስ ፓርክ ዛሬ ተመረቀ !!

Share the Post:

ደቡብ ግሎባል  ባንክ  ከ17 ሚልየን ብር በላይ  ወጪ በማድረግ ያሰራው እጅግ ማራኪና ውብ ፓርክ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አብዱልቃድር፤ የደቡብ ግሎባል ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ዮናስ አያሌው እንዲሁም    የተለያዩ የመንግስት ተወካዮችና የባንካችን ፕሬዝደንት የተከበሩ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩን ጨምሮ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትና ጥሪ  የተደረገላቸው  እንግዶች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት ተመርቋል፡፡ ይህ ፓርክ  በቂርቆስ ክ/ከተማ  የመጀመሪያውና ትልቁ ፓርክ ሲሆን  ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትና ድምቀት ከመሆኑም በላይ በውስጡ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት  በመስጠት ቁጥራቸው ብዙ ለሆኑ ሰዎች የስራ ዕድልን መፍጠር መቻሉ ልዩ ያደርጋል፡፡ ባንካችን  ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ  ሀገራዊ እና ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች ላይ ዘርፈ ብዙ ድጋፎች ያደረገ ሲሆን  ይህንኑ ማህበራዊ ሀላፊነቱን የመወጣት ስራውን በማጠናከር   በዛሬው ቀን አዲስ አበባን የሚመጥን  እጅግ ውብና ማራኪ የሆነ ፓርክ ሰርቶ  ሲያስረክብ  ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና አርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 14 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 13 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ...