ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተከታታይ እያከናወነ የሚገኘው የከፍተኛ ደንበኞችን የስራ እንቅስቃሴ የመጎብኘት ሂደት አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ግብኝታቸውን በሮዜታ ግሩፕ ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም አድርገዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የድርጅታችንን የስራ እንቅስቃሴ በመመልከቱ የተሰማቸውን ደስታ የገለፁት የሮዜታ ግሩፕ መስራችና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው ድርጅታቸው ከባንኩ ጋር እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ድርጅታቸው በበርካታ ቢዝነስ በተለይም በቴክኖሎጅ፣ በሪልስቴት እና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ያመላከቱት አቶ ቴዎድሮስ ከግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ጋር ከዚህ የበለጥ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ሮዜታ ግሩፕ ላደረገላቸው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባባል ምስጋናቸውን ያቀረቡት የባንኩ የቦርድ አባላት እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ድርጅቱ በብዙ ዘርፍ ለሀገር እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።

ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዋነኛ መለያ መሆኑን የገለፁት የባንኩ ኃላፊዎች ፤ ከሮዜታ ግሩፕ ጋር ከወትሮው ላቅ ባለ መልኩ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በጉብኝት መርሃ ግብሩ ባንኩ እና ድርጅቱ በሁለንተናዊ መልኩ  አብረው መስራት በሚችሉበት ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የደንበኞችን የስራ እንቅስቃሴ የመጎብኘት ሂደት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!