Search
Close this search box.

የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

Share the Post:

የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
የ ግሎባል ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 5ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 7 ቀን 2ዐ1ዐ ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የጉባኤው አጀንዳዎች
1. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፣
2. የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅና አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፣
3. የ2ዐ16/17 የዳሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ፣
4. የ2016/17 የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥ፣
5. በቀረቡት የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
6. የ2016/17 የተጣራ ትርፍ ድልድል ላይ ተወያይቶ መወሰን ፣
7. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አበል መወሰን ፣
8. የውጭ ኦዲተሮች መሾምና አበላቸውን መወሰን፣
9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ ሪፖርት ማድመጥ ፣
10. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ፣
11. የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ ፣
ማሳሰቢያ
 በጉባኤው ላይ በአካል መገኝት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ከኢትዮጵያ ሆቴል በስተጀርባ ናሽናል ታወር ከሚገኝው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 9ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት በመቅረብ የውክልና ቅጽ በመሙላት ወይም አግባብ ባለው የመንግስት አካል የተረጋግጠ የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ በመቅረብ የጉባኤው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
 በባንኩ ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባኤው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ኢትዮጵያዊነታችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንደዚሁም አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ ይዛችሁ የምትቀርቡ ተወካዮች የወካዮቻችሁን ኢትዮጵያዊነት የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይንም ፓስፖርት ወይንም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
 በዕለቱ ጉባኤው ተወያይቶ የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች በጉባኤው ባልተገኙ አባላት ላይ ጭምር የፀና ይሆናል፡፡
የ ግሎባል ባንክ አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ

Related Posts