የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የተመረጡትን የደቡብ ግሎባል ባንክ የቦርድ አባላት ምርጫ አጸደቀ

Share the Post:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የተመረጡትን የደቡብ ግሎባል ባንክ የቦርድ አባላት ምርጫ አጸደቀ

(ሚያዚያ 3 ቀን 2010 ዓ.ም)  ግሎባል ባንክ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት ባንኩን እንዲመሩ በባለአክሲዮኖች የተመረጡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አፀደቀ፡፡

ታህሳስ ወር በተደረገው የባለአክሲዮኖች ስብሰባ ከተመረጡት 11 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ውስጥ  8 አዳዲስ እና 3 ነባር የቦርድ አባላት ሲሆኑ፤ ሁሉም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይሁንታ አግኝተዋል፡፡ በዚሁም መሠረት የባንኩ የቦርድ አባላት በመሆን የተመረጡት አቶ ኑረዲን አወል’ አቶ ማቲዎስ አሰሌ’ አቶ ሀብታሙ ሲላ’ አቶ ታሪኩ ኦልጂራ’ አቶ ፍሬው በቀለ’ ዶክተር ተገኔ ሂዋንዶ’ አቶ አክሊሉ ካሳ’ አቶ መላኩ ገዙ’ አቶ ሀይሌ ሀመሮ’ አቶ ግዛው ወ/ሰማያት እና አቶ ታሪኩ ብርሀኑ ናቸው፡፡

አዲሶቹ የቦርድ አባለት ስራ ከመጀመራቸዉ በፊት በሂልተን ሆቴል በተካሄደ ስነስርአት የ “እንኳን ደህና መጣችሁ ” አቀባበል የተደረገላቸዉ ሲሆን ለቀድሞዎቹ የቦርድ አባላት ደግሞ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እዉቅና የሚሰጥ ሽልማት ተበርክቶላቸዉ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡በተለያዩ የስራ መስኮች የካበተ የስራ ልምድ ያላቸዉ አዲሶቹ የቦርድ አባላት፣ ሙያቸዉንና ልምዳቸዉን በመጠቀም ባንኩን ወደ ተሻለ ደረጃ ያሳድጉታል ተብሎ እምነት ተጥሎባቸዋል፡፡

አቶ ኑረዲን አወል  በድጋሚ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ሆነው እንዲያገለግሉ የተመረጡ ሲሆን’ አቶ ኑረዲን በንግድ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ እና ከ25 ዓመት በላይ የተለያዩ የንግድ ሥራዎችን የመምራት ልምድ አላቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የጂሰቨን ኃ.የተ.የግ.ማ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡

————————————— // ————————————

ለተጨማሪ መረጃ የባንኩን የማርኬቲንግና ሪሶርስ ሞቢላይዜሽን መምሪያ ያነጋግሩ፡፡

ስልክ 0115 58 16 23/0115 58 12 45

Related Posts

የሁለት ሚሊዬን ብር ድጋፍ ተደረገ !!!

የሁለት ሚሊዬን ብር ድጋፍ ተደረገ !!! ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ብር ሁለት ሚሊዬን በማዕከሉ...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን በተከሰተው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች 1 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ብር ድጋፍ አደረገ

ባንካችን በቅርቡ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖቻችንን ቦታው ድረስ በመገኘት...