Search
Close this search box.

10ኛው የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

Share the Post:


ከእድገትዎ መሰላል እስከ ለጋራ ስኬታችን!!
                         ‹‹ ከእድገት እስከ ልህቀት ››            

  ግሎባል ባንክ የጀመረውን ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ በማስቀጠል በአሁን ሰአት ከፍተኛ በሆነ የእድገት ጎዳና ላይ ይገኛል፡፡ ባንኩ ባለፉት አስር አመታት ከፍተኛ እድገት እያመጣ ከመሆኑም በላይ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት የቅርንጫፉን ብዛት 136 በማድረስ በመላ
 አገሪቱ ተደራሽ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እንደ እ.ኤ.አ የጊዜ ቀመር በመገባደድ ላይ ባለው የበጀት አመት ማለትም  2021/22  ባንኩ ትርፋማ ከመሆኑም በላይ  ዘመኑን የዋጀ እና በአገልግሎት አሰጣጡ እጅግ ዘመናዊ እንዲሁም  ለአጠቃቀም ምቹና አስተማማኝ  የሆነ የዲጂታል ባንኪንግ አግልግሎት ( ሞባይል ባንኪንግ እና ኢንተርኔት ባንኪንግ ) ለመስጠት የመጨረሻ የሆነውን የትግበራ ስራ  ያጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡም ተግባራዊ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡ በዚህ ብቻ  ሳይወሰን ባንካችን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለወደፊት የዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ የሚሆን ከ 5,500 ካ.ሜ በላይ የሆነ ቦታ ሜክሲኮ በተለምዶ ኬኬር ህንፃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተረክቧል  ፡፡ 
ደቡብ ግሎባል ባንክ በዕለተ ቅዳሜ ታህሳስ 08 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊንየም አዳራሽ ባከናወነው 10ኛ መደበኛና 4ኛ ድንገተኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በከፍተኛ ጥናትና የዘርፉ ባለሙያዎች የተሰራውን የባንኩን የስያሜ ፤ የንግድ ምልክትና የቀለም ለውጥ (Rebranding Work) በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን ጠቅላላ ጉባኤውም የቀረበውን የባንኩን የስያሜ ፤ የንግድ ምልክትና የቀለም ለውጥ በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል ፡፡
በመሆኑም ባንኩ ይህንን የፀደቀውን የባንኩን ስያሜ እንዲሁም የንግድ ምልክትና የቀለም ለውጥ በቅርቡ በይፋ ለመጠቀም እና ለማስተዋወቅ የሚያስችለውን ሒደትና የህግ አግባብ በመፈፀም ላይ ሲሆን በቅርቡም በአዲሱ የባንኩ ስያሜ እንዲሁም የንግድ ምልክትና ቀለም በይፋ ስራ በመጀመር ከእናንተ ክቡራን ደንበኞቹ ጋር በላቀ አገልግሎት እንደሚያገናኝና ስኬቱም የጋራ እንደሚሆን የባንኩ የፀና እምነት ነው ፡፡ 
 
ስለሆነም እርስዎም በሚታይ መልኩ እያደገና ስኬታማ እየሆነ ካለው ባንክ ጋር አብሮ በመስራት የእድገትና የስኬቱ ተጋሪ ይሆኑ ዘንድ ባንኩ በክብር ይጋብዝዎታል፡፡ ለጋራ ስኬታችን አብረን  እንስራ ፡፡
 
  ግሎባል ባንክ !
‹‹ ግሎባል የእድገትዎ መሰላል ›› !!