ደቡብ ግሎባል ባንክ ከ17 ሚልየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያሰራው እጅግ ማራኪና ውብ ፓርክ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አብዱልቃድር፤ የደቡብ ግሎባል ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ዮናስ አያሌው እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት ተወካዮችና የባንካችን ፕሬዝደንት የተከበሩ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩን ጨምሮ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት ተመርቋል፡፡ ይህ ፓርክ በቂርቆስ ክ/ከተማ የመጀመሪያውና ትልቁ ፓርክ ሲሆን ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትና ድምቀት ከመሆኑም በላይ በውስጡ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት በመስጠት ቁጥራቸው ብዙ ለሆኑ ሰዎች የስራ ዕድልን መፍጠር መቻሉ ልዩ ያደርጋል፡፡ ባንካችን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ሀገራዊ እና ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች ላይ ዘርፈ ብዙ ድጋፎች ያደረገ ሲሆን ይህንኑ ማህበራዊ ሀላፊነቱን የመወጣት ስራውን በማጠናከር በዛሬው ቀን አዲስ አበባን የሚመጥን እጅግ ውብና ማራኪ የሆነ ፓርክ ሰርቶ ሲያስረክብ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡