ለስኬታችሁ መዳረሻ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ብርቱ አጋርነት ተጠናክሮ ይቀጥላል – የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ምርት እና አገልግሎቱን እንዲሁም የአሰራር ልህቀቱን ከደንበኞች ጋር የሚያስተዋውቅበት ግሎባል ቱር የተሰኘውን የውይይት መርሐግብር ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ከሚገኙ ደንበኞች ጋር በሴንተራል ሆቴል አከናውኗል። ባንኩ ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በማስተካከል ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ በማጠናከረ ለደንበኞቹ ምቹ እና ቀልጣፍ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የደንበኞች ግንኙነት መምሪያ […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2025 የፈጠራና ልዕቀት ሽልማት አሸናፊ ሆነ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ International Center for Strategic Alliance ባዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም ላይ ምርጥ እያደገ የሚገኝ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት አቅራቢ በመባል ልዩ ሽልማት መቀበሉን ለማብሰር እንወዳለን፡፡ ይህ ሽልማት ከሚያስገኘው ፋይዳ ውጭ፣ የባንካችንን በዲጂታል ዘርፉ እያደረገ ያለውን መልካም ጉዞ የሚያጎላ እንዲሁም ፈጠራ ላይ እና የተሻለ የደንበኞች ዲጂታል አገልግሎትን የሚያበረታታ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ለዚህ ሽልማት እንድንበቃ ላደረጋችሁን የባንካችን […]