ከደንበኞች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው የውይይት መድረክ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል ከደንበኞች ጋር የሚያደርገውን የውይይት መድረክ በጅማ ከተማ ከሚገኙ ደንበኞች ጋር መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም በዶሎሎ ሆቴል አካሂዷል። በውይይት መርሃ ግብሩ የባንኩን የስራ እንቅስቃሴ አስመልክተው የመወያያ ሀሳብ ያቀረቡት የደንበኞች ግንኙነት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ መሰረት አሰፋ ባንኩ በበርካታ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል። በቀረበው የመወያያ ሰነድ መሰረት […]

ሴት ሰራተኞችን በማብቃት  ወደ አመራርነት ማምጣት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሴት ሰራተኞችን በማብቃት ወደ አመራርነት ማምጣት የሚያስችል የስልጠናና የትምህርት መርሃ ግብር መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በይፋ አስጀምሯል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሰራተኞቹን ለማብቃት ዘርፈ ብዙ ስልጠናወችንና ትምህርቶችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ማሞ በአደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አመላክተዋል። በተያዘው የሂሳብ ዓመት 120 ሴት ሰራተኞችን በልዩ […]