ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በቀጣይ አምስት ወራት ሊተገበሩ በሚገቡ አንኳር የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሲያካሄድ የነበረውን ምክክር የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም አጠናቀቀ።

ስብሰባው ለተከታታይ ሁለት ቀናት የባንኩ የቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በኖራ ሪዞርት ተካሂዷል። በምክክር መርሃ ግብሩ የባንኩ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት አጠቃላይ አፈፃፀም እና የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ሊሰሩ በሚገቡ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በባንክ ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ እያጠናከረ እንደሚገኝ የገለፁት የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው፤ በሁሉም መለኪያዎች ተወዳዳሪነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል […]