ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የአርንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርኃግብር አካሄደ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ዙር የአርንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አቢሲኒያ ውሃ ፋብሪካ አካባቢ ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም አካሄዷል፡፡ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል። የዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ግሎባል ባንክ […]
የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች እውቅና ተሰጠ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በ2024/25 የሒሳብ ዓመት ባንኩ ባስቀመጠው የመለኪያ መስፈርት መሠረት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል። በተቀመጠው የመለኪያ መስፈርት መሠረት ከምስራቅ አዲስ አበባ፣ ከምዕራብ አዲስ አበባ እንዲሁም ከደቡባዊ ዲስትሪክት እስከ ሶስት ለወጡ ቅርንጫፎች በባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል። አትላስ፣ አዳማፓንአፍሪክ እና ገላን ኮንደሚኒየም ከምስራቅ አዲስ አበባ […]
በሁሉም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት አስመዝግበናል – ዶ.ር ተስፋየ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በሁሉም የመለኪያ መስፈርቶች የሚበረታታ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ.ር ተስፋዬ ቦሩ ተናገሩ። ዋና ስራ አስፈፃሚው ይኸን ያሉት ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2024/25 የሒሳብ ዓመት አፈፃፀም በገመገመበት እና የ2025/26 የሒሳብ ዓመት ዕቅድ ላይ ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው። በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ተለዋዋጭ የማክሮ […]