ከደንበኞች ጋር እየተካሄደ የሚገኘው ውይይት ተጠናክሮ ቀጥሏል

ግሎባል ቱር በሚል መጠሪያ ከባንካችን ደንበኞች ጋር እየተካሄደ የሚገኘው የውይይት እና የጉብኝተ መርሃ ግብር ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም በአብዲሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ የባንካችን ከፍተኛ ኃላፊዎች ከትሬዲንጉ መስራችና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዲሳ ሚዴቅሳ ጋር ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ግሎባል ቱር በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያለጋራ ስኬታችን