ከከፍተኛ ደንበኞች ጋር እየተካሄደ ያለው ውይይት ተጠናክሮ ቀጥሏል

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከከፍተኛ ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያካሂደውን የጉብኝትና የውይይት መርሃ ግብር አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ባንካችን ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከይርጋጨፌ ቡና ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡  በውይይት መድረኩ የባንካችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የዩኒየኑ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን፤  በባንኩና በዩኒየኑ መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ቀጣይነት ያለው የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የውይይቱ ዋና ዓላማ መሆኑ […]

ግሎባል ቱር ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የደንበኞችን የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም በጋራ ሊሰራባቸው በሚችሉ ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት የሚካሄድበት ግሎባል ቱር በዳዬ በንሳ ቢዝነስ ግሩፕ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም  ተካሂዷል። በውይይቱ የባንካችን ተ/ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳህለሚካኤል መኮንን(ዶ/ር) ጨምሮ የባንካችን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የዳዬ በንሳ ቢዝነስ ግሩፕ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ዱካሞ ከግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ጋር ለረዥም […]