
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የደንበኞችን የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም በጋራ ሊሰራባቸው በሚችሉ ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት የሚካሄድበት ግሎባል ቱር በዳዬ በንሳ ቢዝነስ ግሩፕ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ተካሂዷል።
በውይይቱ የባንካችን ተ/ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳህለሚካኤል መኮንን(ዶ/ር) ጨምሮ የባንካችን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።



የዳዬ በንሳ ቢዝነስ ግሩፕ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ዱካሞ ከግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ጋር ለረዥም ጊዜ ሲሰሩ መቆየታቸውን አውስተው ወደፊትም ከባንኩ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የባንካችንን ደንበኞች የስራ እንቅስቃሴ የሚጎበኝበት እና ውይይት የሚደረግበት ግሎባል ቱር በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን