ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር ዋነኛ መርህ አድርጎ እየሰራ ነው – ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማጠናከር ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት ዋና ዕሴት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ገለጹ፡፡ ዶ/ር ተስፋዬ ይኸን ያሉት ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን የሥራ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እና የንግድ እንቅስቃሴያቸውን በቅርብ መከታተል የሚያስችለውን ግሎባል ቱር የተሰኘውን የጉብኝት መርሃ ግብር በዳዬ በንሳ ቢዝነስ […]

ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ዉጤት መመዝገቡ ተገለፀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በበርካታ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ የቦርድ አመራር እና የማኔጅመንት አባላት ገለጹ፡፡ ይህ የተገለጸው የቦርድ አመራሮችና ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት የ2025/26 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ሚያዚያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ባካሄዱበት ወቅት ነው፡፡ የተቀማጭ ገንዘብ መጠንን ማሳደግ፣ የብድር አሰጣጥ እና የትርፍ ግቦችን ማሳካት፣ የባንኩን […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተሳተፈበት ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ነህሚያ የኦቲዝም ማዕከል የ2018 ዓ.ም የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብርን ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች አከናውኗል። መርሃ-ግብሩ በዋናነት በህብረተሰቡ ዘንድ ስለ ኦቲዝም ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ በኦቲዝም የተጠቁ ህጻናት ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙ ለማስገንዘብ ታልሞ መዘጋጀቱን የማዕከሉ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ራሄል አባይነህ ገልጸዋል። መርሃ-ግብር የተሳካ እንዲሆንና የታለመለትን አላማ እንዲያሳካ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ ለደንበኞቹ የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የመተሳሰብ ተምሳሌት የሆነውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ በድሬዳዋ ከተማ ለሚገኙ ደንበኞች የኢፍጣር መርሃ-ግብር መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል። በዝግጅቱ ላይ የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ በድሬዳዋ ከተማ የሚገኙ ደንበኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የከተማዋ መጅሊስ ተወካዮች ታድመዋል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከንግድ እንቅስቃሴው ባሻገር ማህበራዊና ሃይማኖታዊ እሴቶችን ማክበርና ከደንበኞቹ ጋር ያለውን መልካም ትስስር […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በጅማ ከተማ ለሚገኙ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ

1447ኛውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም  በለይሌ ሪዞርት በተሰናደው የኢፍጣር መርሃ ግብር የባንካችን ኃላፊዎች፣ ደንበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የደንበኞችን ፍላጎት ማዕከል ያደረግ ምቹ እና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ወቅት የገለፁት ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን በቀጣይም የደንበኞቻችንን ፍላጎት የሚያሟላ አገልግሎት ለመስጠት […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከጅማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጋር በጋራ መስራት በሚቻልበት ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት አደረገ።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና የጅማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በተለያዩ ዘርፎች በጋራ መስራት በሚቻልበት ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ የሁለቱም ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት መጋቢት 06 ቀን 2018 ዓ.ም በመጅሊሱ ዋና ጽ/ቤት ተወያይተዋል። በውይይቱ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታውች ላይ ያጠነጠነ ሲሆን በተለይ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፍ እና ተደራሽ በሚሆንበት ዙሪያ በጥልቀት ውይይት አድርገዋል። በጅማ ከተማ […]

ባንካችን በጅማ ከተማ ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ 1447ኛውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ በጅማ ከተማ ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ አካላት ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በቡካሪ መስጂድ  አከናውኗል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት የባንኩ ዋነኛ እሴት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት የባንካችን ኮርፖሬት ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን ዛሬ ያካሄድነው ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ይኸንኑ ዕሴት […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በየሲር ለና በጎ አድራጎት ድርጅት የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቅዱስ የሆነውን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰርለና በጎ አድራጎት ድርጅት የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ ባንካችን ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን ይኸን መሰል የበጎ አድራጎት ተግባራትን ለረዥም ጊዜ እያከናወነ እንደሚገኝ የገለጹት የማርኬቲንግና እና ኮምዩኒኬሽስ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ በተለያዩ ጊዜ ባንኩ የሚያደርጋቸው ድጋፎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል፡፡ የረመዳን ወር […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በቀጣይ አምስት ወራት ሊተገበሩ በሚገቡ አንኳር የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሲያካሄድ የነበረውን ምክክር የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም አጠናቀቀ።

ስብሰባው ለተከታታይ ሁለት ቀናት የባንኩ የቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በኖራ ሪዞርት ተካሂዷል። በምክክር መርሃ ግብሩ የባንኩ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት አጠቃላይ አፈፃፀም እና የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ሊሰሩ በሚገቡ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በባንክ ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ እያጠናከረ እንደሚገኝ የገለፁት የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው፤ በሁሉም መለኪያዎች ተወዳዳሪነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር ያለውን የስራ ትብብር ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄደ።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) ጋር ያለውን የስራ ትብብር አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስችል ውይይት ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም አከናውኗል። የዛሬው ውይይት ከዚህ በፊት በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘውን የደንበኞችን የስራ እንቅስቃሴ የመጎብኘት መርሃ ግብር አንዱ አካል ነው። በውይይቱ ባንኩ እና ኮርፖሬሽኑ ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ምቹ […]

በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት አመርቂ ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ባንኩ ባስቀመጣቸው መለኪያዎች መሰረት የሚበረታታ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ የቦርድ እና የማኔጅመንት ዓባላት ገለፁ፡፡ የባንኩ የቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት ያለፉት ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀምን ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ገምግመዋል፡፡ የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ፣ የብድር አቅርቦት፣ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ማስፋፋት፣ የደንበኞች እርካታን ማሻሻል እና ትርፋማነትን በማጠናከር […]

በላቀ አመራር ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በላቀ የአመራር ሰጭነት Advanced Leadership Training ዙሪያ ለባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት በስካይ ላይት ሆቴል ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም አጠናቋል፡፡ ስልጠናው ከአልቲሜት የማማከር አገልግሎት ጋር በመተባበር የተሰጠ ሲሆን የባንኩን ሁለንተናዊ የአመራር አቅም ይበልጥ ለማጠናከር፣ የውሳኔ አሰጣጥ ጥራትን ለማሻሻል እና በተለዋዋጭ የባንክና የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ በተቀመጡ መለኪያዎች […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በሆራ ኮርፖሬት ግሩፕ የመስክ ምልከታ አካሄደ።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ግሎባል ቱር” በተሰኘ መሪ ቃል እያካሄደ የሚገኘውን የባንኩን ከፍተኛ ደንበኞች እና ባለድርሻ አካላት የመጎብኘት መርሃ ግብር አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። ግሎባል ቱር በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ሲሆን ጥር 09 ቀን 2018 ዓ.ም በሆራ ኮርፖሬት ግሩፕ የመስክ ምልከታ ተደርጓል። የባንኩ ኃላፊዎችና የቦርድ አባላት የኮርፖሬት ግሩፑን ሁለንተናዊ የስራ እንቅስቃሴ በመስክ ምልከታ በመጎብኘታቸው ምስጋናቸውን […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ ብርቱ አጋር መሆኑን አጠናክሮ ይቀጥላል – አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን (ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር)

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ የስኬት መዳረሻ ብርቱ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል የባንኩ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን ገለፁ። አቶ ሳኅለሚካኤል ይኸን ያሉት ሮዜታ ሪል እስቴት ከግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተደረገለት የፋይናንስ ድጋፍ የንግድ ሱቆቹን እና አፓርትመንቶችን በድሬዳዋ ከተማ ገንብቶ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ለሽያጭ ባቀረበበት ወቅት ነው። የተገነቡት የንግድ ሱቆች ዘመናዊ ዲዛይንና ለንግድ ሥራ […]

ከፍተኛ ደንበኞችን የመጎብኘት ሂደት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል እያካሄደ ያለውን የባንኩን ከፍተኛ ደንበኞች የመጎብኘት እና የውይይት መርሃ ግብር አጠናክሮ ቀጥሏል። የጉብኝት መርሃ ግብሩ ታኅሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአርፋሳ ጠቅላላ ንግድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ተከናውኗል። በጉብኝት መርሃ ግብሩ የባንካችን የቦርድ አባላት እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአርፋሳ ጠቅላላ ንግድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ጋር በርካታ ዓመታትን አብረው […]

በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች ዕውቅና ተሰጠ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት በተለያዩ የስራ መለኪያዎች የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ በመቐለ እና አካባቢው ለሚገኙ ቅርንጫፎች ታኅሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በፕላኔት ሆቴል የዕውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል። በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ስድስት ወራት የሚበረታታ ስራ መከወኑን በዕውቅና መርሃ ግብሩ ወቅት የገለፁት የምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ግርማ፤ በሁለተኛው መንፈቅ ዓመትም ሁሉም ቅርንጫፎች […]

በሁለንተናዊ ዘርፍ ምርጡ ባንክ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ ነው – አቶ ውብሸት ዘገዬ (ቺፍ ሪቴል ባንኪንግ ኦፊሰር)

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ፋይናንስ ነክ በሆኑና ባልሆኑ መለኪያዎች በደንበኞች ዘንድ የመጀመሪያ ተመራጭ እና ምርጡ ባንክ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የባንኩ ቺፍ ሪቴል ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ውብሸት ዘገዬ ገለፁ፡፡ ቺፍ ኦፊሰሩ ይህን ያሉት ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች እና ሰራተኞች የዕውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር ታኅሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በሀያት […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በቀርጫንሼ ግሩፕ የጉብኝት መርሃ ግብር አካሄደ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ግሎባል ቱር” በሚል መሪቃል የሚያካሂደውን የደንበኞችን የስራ እንቅስቃሴ የመጎብኘት እና የውይይት መርሃ ግብር ታኅሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በቀርጫንሼ ግሩፕ አካሂዷል። በጉብኝት መርሃ ግብሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው፣ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ፣ የቦርድ አባላት፣ ቺፍ ኦፊሰሮች እና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ቀርጫንሼ ግሩፕ አብረው […]

ከፍተኛ ደንበኞችን የመጎብኝት ሂደት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተከታታይ እያከናወነ የሚገኘው የከፍተኛ ደንበኞችን የስራ እንቅስቃሴ የመጎብኘት ሂደት አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ግብኝታቸውን በሮዜታ ግሩፕ ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም አድርገዋል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የድርጅታችንን የስራ እንቅስቃሴ በመመልከቱ የተሰማቸውን ደስታ የገለፁት የሮዜታ ግሩፕ መስራችና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው ድርጅታቸው ከባንኩ ጋር እየሰራ ያለውን ስራ […]

በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው የተመራ ልዑክ በቶፕ ቢቬሬጅ እና ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ ጉብኝት አካሄደ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው የተመራ ልዑክ በቶፕ ቢቬሬጅ እና ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ ኅዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም የጉብኝት መርሃ ግብር አከናውኗል፡፡ በጉብኝቱ የባንኩ የቦርድ አባላት፣ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ እንዲሁም ቺፍ ኦፊሰሮች እና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ዛሬ የተካሄደው የጉብኝት መርሃ ግብር ግሎባል ቱር በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባና […]

ከደንበኞች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው የውይይት መድረክ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል ከደንበኞች ጋር የሚያደርገውን የውይይት መድረክ በጅማ ከተማ ከሚገኙ ደንበኞች ጋር መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም በዶሎሎ ሆቴል አካሂዷል። በውይይት መርሃ ግብሩ የባንኩን የስራ እንቅስቃሴ አስመልክተው የመወያያ ሀሳብ ያቀረቡት የደንበኞች ግንኙነት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ መሰረት አሰፋ ባንኩ በበርካታ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል። በቀረበው የመወያያ ሰነድ መሰረት […]

ሴት ሰራተኞችን በማብቃት  ወደ አመራርነት ማምጣት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሴት ሰራተኞችን በማብቃት ወደ አመራርነት ማምጣት የሚያስችል የስልጠናና የትምህርት መርሃ ግብር መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በይፋ አስጀምሯል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሰራተኞቹን ለማብቃት ዘርፈ ብዙ ስልጠናወችንና ትምህርቶችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ማሞ በአደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አመላክተዋል። በተያዘው የሂሳብ ዓመት 120 ሴት ሰራተኞችን በልዩ […]

የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄደ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ደምና ሕብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር ነሀሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡ “አዲሱን ዓመት በበጎ ስራ እንቀበለው” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብር የባንካችን ሰራተኞች እና አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን የደም ልገሳ […]

ለስኬታችሁ መዳረሻ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ብርቱ አጋርነት ተጠናክሮ ይቀጥላል – የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ምርት እና አገልግሎቱን እንዲሁም የአሰራር ልህቀቱን ከደንበኞች ጋር የሚያስተዋውቅበት ግሎባል ቱር የተሰኘውን የውይይት መርሐግብር ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ከሚገኙ ደንበኞች ጋር በሴንተራል ሆቴል አከናውኗል። ባንኩ ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በማስተካከል ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ በማጠናከረ ለደንበኞቹ ምቹ እና ቀልጣፍ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የደንበኞች ግንኙነት መምሪያ […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2025 የፈጠራና ልዕቀት ሽልማት አሸናፊ ሆነ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ International Center for Strategic Alliance ባዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም ላይ ምርጥ እያደገ የሚገኝ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት አቅራቢ በመባል ልዩ ሽልማት መቀበሉን ለማብሰር እንወዳለን፡፡ ይህ ሽልማት ከሚያስገኘው ፋይዳ ውጭ፣ የባንካችንን በዲጂታል ዘርፉ እያደረገ ያለውን መልካም ጉዞ የሚያጎላ እንዲሁም ፈጠራ ላይ እና የተሻለ የደንበኞች ዲጂታል አገልግሎትን የሚያበረታታ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ለዚህ ሽልማት እንድንበቃ ላደረጋችሁን የባንካችን […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የአርንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርኃግብር አካሄደ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ዙር የአርንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አቢሲኒያ ውሃ ፋብሪካ አካባቢ ሐምሌ 28  ቀን 2017 ዓ.ም አካሄዷል፡፡ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል። የዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ግሎባል ባንክ […]

የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች እውቅና ተሰጠ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በ2024/25 የሒሳብ ዓመት ባንኩ ባስቀመጠው የመለኪያ መስፈርት መሠረት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል። በተቀመጠው የመለኪያ መስፈርት መሠረት ከምስራቅ አዲስ አበባ፣ ከምዕራብ አዲስ አበባ እንዲሁም ከደቡባዊ ዲስትሪክት እስከ ሶስት ለወጡ ቅርንጫፎች በባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል። አትላስ፣ አዳማፓንአፍሪክ እና ገላን ኮንደሚኒየም ከምስራቅ አዲስ አበባ […]

በሁሉም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት አስመዝግበናል – ዶ.ር ተስፋየ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በሁሉም የመለኪያ መስፈርቶች የሚበረታታ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ.ር ተስፋዬ ቦሩ ተናገሩ። ዋና ስራ አስፈፃሚው ይኸን ያሉት ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2024/25 የሒሳብ ዓመት አፈፃፀም በገመገመበት እና የ2025/26 የሒሳብ ዓመት ዕቅድ ላይ ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው። በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ተለዋዋጭ የማክሮ […]

ዲጂታል የኢንሹራንስ እና የአረቦን ብድር አገልግሎት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከኒያላ ኢንሹራንስ እና ከካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ጋር በመተባበር ዲጂታል የኢንሹራንስ እና የአረቦን ብድር አገልግሎትን ሀምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ አስጀምሯል፡፡ በመርሃ ግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዲጂታል ባንኪንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ መቅደስ በቀለ፣ የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ቺፍ ከስተመር ማኔጅመንት ኦፊሰር አቶ ተገኝ ማስረሻ፣ የካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሀም […]

ለስኬታችሁ ብርቱ አጋር መሆናችንን አጠናክረን እንቀጥላለን – አቶ ሳኅለሚካኤል መኮነን

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለደንበኞች የስኬት መዳረሻ  ብርቱ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል የባንኩ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮነን ገለፁ። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የባንኩን የስራ እንቅስቃሴ ከደንበኞቹ ጋር የሚያስተዋውቅበት “ግሎባል ቱር” የተሰኘውን የውይይት መርሃ ግብር በድሬዳዋ ከተማ ከሚገኙ ደንበኞች ጋር  ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በኢስት ስታር ሆቴል አከናውኗል። በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት በሁሉም መመዘኛዎች አመርቂ ውጤት […]

የደንበኞቻችንን ፍላጎት ያማከለ የባንክ አገልግሎት እየተሰጠ ነው – አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የደንበኞቹን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎት በመላው የሀገራችን ክፍል እየሰጠ መሆኑን የባንኩ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን ገለፁ። አቶ ሳኅለሚካኤል ይኸን ያሉት “ግሎባል ቱር” በሚል መሪቃል በአሶሳ ከተማ ከሚገኙ ደንበኞች ጋር ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ በአደረጉት የውይይት መርሃ ግብር ነው። በባንኩ እና በደንበኞች መካከል እንደ […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለስድስት ተከታታይ ወራት ያሰለጠናቸውን ከ70 በላይ ሠራተኞች አስመረቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “በሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎት አሰጣጥ” ዙሪያ ለስድስት ተከታታይ ወራት ያሰለጠናቸውን ሠራተኞች ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ- ስርዓቱ ላይ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቺፍ ፋይናንስ እና ሰፖርት ኦፊሰር አቶ ዳሳ ጎቤ፣ ቺፍ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ኦፊሰር አቶ ሲሳይ አየለ እንዲሁም የባንኩ የማኔጅመንት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል። ስልጠናው […]

በተሰለፈበት ሁሉ ማሸነፍ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ መለያ እንዲሆን እየተሰራ ነው – ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተሰማራበት የሥራ ዘርፍ ሁሉ ቀዳሚ እና አሸናፊ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ተናገሩ፡፡ ዶ/ር ተስፋዬ ይኸን ያሉት ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ምርጥ የቁጠባ ባንክ ዘርፍ ተሸላሚ መሆኑንና የባንኩ የእግር ኳስ ቡድን የ2017 ዓ.ም የባንኮች እግር ኳስ ውድድርን በበላይነት ማጠናቀቁን አስመልክቶ ዋንጫውን ለዋና ሥራ አስፈፃሚው ሰኔ […]

ግሎባል ቱር በሽረ እንደስላሴ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሄደ።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና አጠቃላይ የባንኩን ነባራዊ ሁኔታ ለደንበኞቹ የሚያስተዋውቅበት “ግሎባል ቱር” የተሰኘውን መርሃግብር በሽረ እንደስላሴ ከተማ በሚገኘው ቅርንጫፍ በተለያዩ ዝግጅቶች ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በድምቀት አካሂዷል። ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ስሙን የሚመጥን አገልግሎት በመላው የሀገራችን ክፍል እየሰጠ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ወቅት ባደረጉት ንግግር የገለፁት የኮርፖሬት ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሳህለሚካኤል መኮንን አዳዲስ […]

ለአዲሱ የቦርድ ሥራ አመራር አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር ተካሄደ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዲስ ለተመረጡ የቦርድ ሥራ አመራር አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ እና ሥራ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ሰኔ 09 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት አካሂዷል፡፡ ባንኩ ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በማረም እና ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል በማይናወጥ የእድገት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የገለጹት የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ምርጥ የቁጠባ ባንክ ዘርፍ አሸናፊ ሆነ

የአፍሪካ የባንክ እና ኢንሹራንስ ሽልማት በታንዛኒያ ዋና ከተማ ዳሬሰላም በተለያዩ ዘርፎች የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ባንኮች እና ኢንሹራንሶች የሽማልት ሥነ ስርዓት ሰኔ 06 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ በአፍሪካ የባንክ እና ኢንሹራንስ ሽልማት ላይ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ምርጥ የቁጠባ ባንክ ዘርፍ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ተመራማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡፡ ግሎባል ባንክ […]

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመደካሞች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ሚያዚያ 09 ቀን 2017 ዓ.ም በሜክሲኮ ፕሪሚየም ቅርንጫፍ ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወረዳ አምስት እና በወረዳ ሰባት ኗሪ የሆኑና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩ […]

የሁለት ሚሊዬን ብር ድጋፍ ተደረገ !!!

የሁለት ሚሊዬን ብር ድጋፍ ተደረገ !!! ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ብር ሁለት ሚሊዬን በማዕከሉ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድጋፍ እና ጉብኝት አድርጓል፡፡ “ለህብረተሰቡ መስጠት” የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አንዱ ዕሴት መሆኑን ድጋፉን ባበረከቱበት ወቅት ያወሱት የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳህለሚካኤል መኮንን የዛሬው […]

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን በተከሰተው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች 1 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ብር ድጋፍ አደረገ

ባንካችን በቅርቡ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖቻችንን ቦታው ድረስ በመገኘት እንደወትሮው ሁሉ አጋርነቱን ከማሳየቱም ባሻገር የተጎዱ ወገኖቻችንን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚደረገው ድጋፍ ለማገዝ የብር 1,500,000.00 ድጋፍ አድርጓል። ይህ ማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ስራ መጨረሻችን ሳይሆን በቀጣይም ወገኖቻችንን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው እንቃስቃሴ ሁሉ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ […]