ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ዉጤት መመዝገቡ ተገለፀ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በበርካታ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ የቦርድ አመራር እና የማኔጅመንት አባላት ገለጹ፡፡

ይህ የተገለጸው የቦርድ አመራሮችና ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት የ2025/26 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ሚያዚያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ባካሄዱበት ወቅት ነው፡፡

የተቀማጭ ገንዘብ መጠንን ማሳደግ፣ የብድር አሰጣጥ እና የትርፍ ግቦችን ማሳካት፣ የባንኩን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ተደራሽነት ማስፋፋት እና የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንደነበረ በግምገማው ወቅት ተገልጿል፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በመድረኩ ወቅት የተነገረ ሲሆን የታዩ ድክመቶችንም በመለየት የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ በፊት ማክሰም እንደሚገባ በአፅንዖት ተነግሯል፡፡

የሀብት ማሰባሰብ ስራን ይበልጥ ማጠናከር፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ማሳደግ፣የአገልግሎት ጥራትንና የዲጂታል አማራጮችን ለደንበኞች ይበልጥ ተደራሽ ማድረግ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በግምገማ መርሃ ግብሩ የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው፣ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ፣ የቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2025/26 የሥራ አፈጻጸምን ገምግሞ ለ2026/27 ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2025/26 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም የገመገመበትን መርሃ ግብር ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር ዋነኛ መርህ አድርጎ እየሰራ ነው – ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማጠናከር ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት ዋና ዕሴት አድርጎ እየሰራ መሆኑን...

ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ዉጤት መመዝገቡ ተገለፀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በበርካታ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ የቦርድ አመራር እና የማኔጅመንት አባላት ገለጹ፡፡...