
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማጠናከር ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት ዋና ዕሴት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ገለጹ፡፡
ዶ/ር ተስፋዬ ይኸን ያሉት ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን የሥራ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እና የንግድ እንቅስቃሴያቸውን በቅርብ መከታተል የሚያስችለውን ግሎባል ቱር የተሰኘውን የጉብኝት መርሃ ግብር በዳዬ በንሳ ቢዝነስ ግሩፕ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በቢሮ ብቻ ሳይወሰን የግሩፑን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት በመምጣቱ ምስጋናቸውን ያቀረቡት የዳዬ በንሳ ቢዝነስ ግሩፕ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ዱካሞ፤ ከባንኩ ጋር ለረዥም ጊዜ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ግሩፕ በበርካታ የስራ መስኮች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ አሰፋ፤ በተለይም በቡና ምርት፣በአስመጪና ላኪነት፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በሪልስቴት እና በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል ፡፡


ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ግሩፕ የባንካችን ደንበኛ ብቻ ሳይሆን መስራችና ባለድርሻ አካል ጭምር መሆኑ በጉብኝት መርሃ ግብሩ ወቅት የተገለጸ ሲሆን የነበረውን የረዥም ጊዜ ደንበኝነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባም ተገልጿል፡፡
በባንኩ እና ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ግሩፕ መካከል ያለውን የፋይናንስ አጋርነት በማጠናከር፣ ሁለቱም ተቋማት የጋራ ስኬት እንዲያስመዘግቡ ማስቻል የጉብኝቱ ዋና ዓላማ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እንደ ዳዬ በንሳ ያሉ ግዙፍ የሀገር በቀል ድርጅቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ተወዳዳሪነት እንዲያሳድጉ አስፈላጊውን የባንክ አገልግሎትና ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የገለጹት ዶ/ር ተስፋዬ፤ በቀጣይም የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያልተቆጠበ ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ፈጣን፣ ዘመናዊ እና ተደራሽ የፋይናንስ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል የባንኩን ከፍተኛ ደንበኞች እና ባለድርሻ አካላት የመጎብኘት መርሃ ግብር በቀጣይም ተጠናከሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!