ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተሳተፈበት ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

Share the Post:

ነህሚያ የኦቲዝም ማዕከል የ2018 ዓ.ም የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብርን ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች አከናውኗል።

መርሃ-ግብሩ በዋናነት በህብረተሰቡ ዘንድ ስለ ኦቲዝም ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ በኦቲዝም የተጠቁ ህጻናት ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙ ለማስገንዘብ ታልሞ መዘጋጀቱን የማዕከሉ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ራሄል አባይነህ ገልጸዋል።

መርሃ-ግብር የተሳካ እንዲሆንና የታለመለትን አላማ እንዲያሳካ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን የኮምዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራ አስኪያጅ አቶ ተመስገን ፍቃዱ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር አመላክተዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከተቋቋመበት ዓላማ በተጨማሪ መሰል ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት መሳተፍ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ተመስገን ለነህሚያ ኦቲዝም ማዕከል ያደረገው ድጋፍም ይህንኑ ዕሴት የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።

ባንኩ ላሳየው አጋርነት ምስጋናቸውን ያቀረቡት ወ/ሮ ራሄል መሰል ድጋፎች ማዕከሉ ለህጻናቱ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማጠናከር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ እንዲሁም በማዕከሉ ለ17ኛ ጊዜ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር የተከናወነ ሲሆን በማዕከሉ ትምህርታቸውን ተከታትለው ወደ መደበኛ ት/ቤት የሚሸኙ ህፃናት የተለያዩ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እና ድርጅቶች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ሲሆን ወደፊትም ማህበራዊ ኃላፊነት የመወጣት ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2025/26 የሥራ አፈጻጸምን ገምግሞ ለ2026/27 ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2025/26 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም የገመገመበትን መርሃ ግብር ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር ዋነኛ መርህ አድርጎ እየሰራ ነው – ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማጠናከር ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት ዋና ዕሴት አድርጎ እየሰራ መሆኑን...

ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ዉጤት መመዝገቡ ተገለፀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በበርካታ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ የቦርድ አመራር እና የማኔጅመንት አባላት ገለጹ፡፡...