ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው፣ ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳኅለሚካኤል መኮንን (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም በባንካችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
 
ባንካችንን በአዲስ መልክ የተቀላቀሉት ወ/ሮ ሌንሴ ገለታ የሪቴል ባንኪንግ እና ሀብት ማሰባሰብ ቺፍ ኦፊሰር እንዲሁም ካሳ ሚኮሮ (ዶ/ር) የፋይናንስ እና ትሬዠሪ ቺፍ ኦፊሰር ሆነው ኃላፊነታቸውን ተረክበዋል።
 
ባንኩ እያከናወነ ያለውን የለውጥ እና የዕድገት ስራዎች ለማሳካት ብቁ የሆኑ የማኔጅመንት አባላትን ማጠናከር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ወቅት የጠቆሙት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው፣ አዳዲሶቹ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የባንኩን አጠቃላይ ተወዳዳሪነት እና አሰራር ይበልጥ በማጠናከር ለባንኩ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
 
ለባንካችን ዕድገት የሰው ኃይሉን በዕውቀትና በክህሎት ማብቃት የማያቋርጥ ትኩረት ሆኖ እንደሚቀጥል የገለፁት ደግሞ የባንካችን ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳኅለሚካኤል መኮንን(ዶ/ር) ናቸው፡፡ አዳዲሶቹ ኃላፊዎች ከነባሩ አመራር እና ሠራተኞች ጋር በመቀናጀት ባንካችንን ወደ ላቀ የስኬት ምዕራፍ ማሻገር እንደሚችሉ ያላቸውን እምነት ተ/ስራ አስፈፃሚው አክለዋል፡፡

ባንኩ ያስቀመጣቸውን ስትራቴጂካዊ ግቦች ለማሳካት እና የደንበኞችን አገልግሎት ጥራት ከፍ ለማድረግ ከቦርዱ፣ ከማኔጅመንቱ እና ከሰራተኞች ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኞች መሆናቸውን ባንካችንን የተቀላቀሉ አዳዲስ የሥራ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ስድስት ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን በ3ኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) አስተምሮ አስመርቋል። ባንካችን በዘመናዊና በሳይንሳዊ ምርምር የተደገፈ የባንክ አሰራርን እውን ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ማለትም በባንኪንግ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በቢዝነስ ሊደርሺፕ እና በቴክኖሎጂ የተመረኩት ከፍተኛ ኃላፊዎች፤ ያከማቹትን ጥልቅ ዕውቀትና የምርምር ክህሎት ወደ ሥራ በመተርጎም የባንኩን ሁለንተናዊ ግብ ማሳካት እንደሚገባ በመርሃ ግብሩ ወቅት አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዲስ ለተሾሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው እየተመኘ፣ በዶክትሬት ዲግሪ ለተመረቁ የባንኩ ኃላፊዎች የተሰማውን ደስታ ይገልጻል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 13 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ...

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሪሞን ጀነራል ትሬዲንግን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ተ/ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሳኅለሚካኤል መኮንን የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ፣ የሪሞን ጀነራል ትሬዲንግን የሥራ...