
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቶፕ ቢቨሬጅ እና ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ጉብኝት እና ውይይት አካሂደዋል።
በጉብኝቱ ላይ የባንካችን ተጠባባቂ ስራ አስፈፃሚ ሳህለሚካኤል መኮንን (ዶ/ር)፣ ቺፍ ኦፊሰሮች እንዲሁም የመምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ቶፕ ቢቨሬጅ እና ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ በበርካታ የስራ ዘርፎች በመሰማራት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው።



የድርጅቱን የምርት ሂደት፣ የአሰራር ስርዓት እና የስራ እንቅስቃሴ በአካል የተመለከቱት የባንካችን ኃላፊዎች፣ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለው ስትራቴጂካዊ አጋርነት ተጠናክሮ መቀጠል የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል፡፡
ከባንካችን ደንበኞች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የሚካሄደው የጉብኝት እና የውይይት መድረክ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን