
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም በግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት አካሂደዋል፡፡
በውይይቱ የሁለቱን ተቋማት አብሮነት ይበልጥ ለማጠናከር እና በቀጣይ ለጋራ ስኬት አብሮ መስራት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ መክረዋል። ባለፉት ጊዜያት ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት አዲስ ምዕራፍ መክፈት እንደሚገባም ተመላክቷል።



ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ የገለጹት የግሩፑ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን መንገሻ፤ ከግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ጋር በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በውይይቱ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ተ/ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳህለሚካኤል መኮንን (ዶ/ር) ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን