ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2025/26 የሥራ አፈጻጸምን ገምግሞ ለ2026/27 ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2025/26 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም የገመገመበትን መርሃ ግብር ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል አከናውኗል።

ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት ባስቀመጣቸው ቁልፍ መለኪያዎች ማለትም፦የተቀማጭ ገንዘብ ዕድገት፣ የብድር አሰጣጥ እና የአመላለስ አፈጻጸም፣ የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነት እና የደንበኞች እርካታ ዙሪያ የተመዘገቡ ውጤቶች በጥልቀት ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ወቅት የተመዘገቡ ውጤቶች ከመገምገማቸው ባሻገር በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የአሰራር ክፍተቶች በግልጽ ተለይተው ተግባራዊ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

የደንበኞችን እርካታ ይበልጥ ማሳደግ፣ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን ማስፋፋት እና የአጠቃላይ ሥራ አፈጻጸም ውጤታማነትን ማረጋገጥ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸው በግምገማው ወቅት ተመልክቷል።

ለ2026/27 በጀት ዓመት እንዲሰሩ የተነደፉ ዕቅዶችን እውን ለማድረግ ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኞች መሆናቸውን የባንካችን ከፍተኛ አመራሮች በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች እና የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ደንበኞቹንና ባለድርሻ አካላትን ማዕከል ያደረገ ዘመናዊ፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው የባንክ አገልግሎት በማቅረብ በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ያለውን ተወዳዳሪነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን

Related Posts

ከባለአክሲዮኖች ጋር የሚደረገው የውይይት መድረክ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከባለአክሲዮኖቹ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችለውን የውይይት መድረክ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም...

ባንኩ የተቋቋመበትን ዓላማ እንዲያሳካ ያልተቆጠበ ድጋፍ እናደርጋለን – ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ባንኩ የተጣለበትን ሀገራዊ እና ማህበራዊ ኃላፊነት በተሟላ ሁኔታ ተወጥቶ የተቋቋመበትን ዓላማ እውን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በእንጦጦ ተራራ...