ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

Share the Post:

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በእንጦጦ ተራራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡

ባንካችን ማህበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ተግባሩን ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፣ የዘንድሮው መርሃ ግብር ለስምንተኛ ጊዜ የተከናወነ ነው። በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በርካታ ሀገር በቀል እና ልዩ ልዩ የፍራፍሬ ችግኞች ተተክለዋል።

ባንካችን ከሚሰጠው የፋይናንስ አገልግሎት በተጨማሪ ለማህበረሰብ እና ለአካባቢ ጥበቃ የሚሰጠውን ማህበራዊ ኃላፊነት በቁርጠኝነት እየተወጣ እንደሚገኝ የገለጹት የማርኬቲንግና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ፤ የተተከሉት ሀገር በቀልና የፍራፍሬ ችግኞች ለአየር ንብረት ለውጥና ብክለት መፍትሔ እንዲሆኑ አስፈላጊው ክትትልና እንክብካቤ ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፉን አረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ መርሃ ግብር በመደገፍ በተከታታይ ስምንት ዓመታት በርካታ ችግኞችን በመትከል ለአካባቢ ጥበቃ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና አርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 14 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 13 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ...