ከባለአክሲዮኖች ጋር የሚደረገው የውይይት መድረክ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከባለአክሲዮኖቹ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችለውን የውይይት መድረክ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት አካሂዷል፡፡

መድረኩ ባለአክሲዮኖች ስለ ባንኩ ወቅታዊ የፋይናንስ አፈጻጸም፣ የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችና አጠቃላይ እድገት ግልጽ መረጃ የሚያገኙበት፤ እንዲሁም አስተያየትና ጥያቄዎቻቸውን በቀጥታ ለከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሚያቀርቡበት ነው፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከባለአክሲዮኖቹ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ማጠናከሩ፣ በባንኩ እና በባለአክሲዮኖቹ መካከል ያለውን እምነት ለማሳደግ እና ርዕዩን ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።

የባንካችን ተ/ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን እና ከፍተኛ አመራሮች ከባለአክሲዮኖች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የባንኩን ዘላቂ እድገትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረጉ ተመሳሳይ ውይይቶች በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና አርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 14 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 13 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ...