
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ደምና ሕብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር ነሀሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡
“አዲሱን ዓመት በበጎ ስራ እንቀበለው” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብር የባንካችን ሰራተኞች እና አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡





ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን የደም ልገሳ ፕሮግራም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡
ባንካችን በቀጣይም ማህበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ተግባሩን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!