በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው የተመራ ልዑክ በቶፕ ቢቬሬጅ እና ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ ጉብኝት አካሄደ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው የተመራ ልዑክ በቶፕ ቢቬሬጅ እና ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ ኅዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም የጉብኝት መርሃ ግብር አከናውኗል፡፡

በጉብኝቱ የባንኩ የቦርድ አባላት፣ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ እንዲሁም ቺፍ ኦፊሰሮች እና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዛሬ የተካሄደው የጉብኝት መርሃ ግብር ግሎባል ቱር በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ከደንበኞች ጋር እየተካሄደ ያለው የውይይት መድረክ አንዱ አካል መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ከባንካችን ጋር የሚሰሩ የድርጅቶች እና የግለሰቦች ስኬት የባንኩም ስኬት መሆኑን በውይይት መርሃ ግብሩ ወቅት የገለፁት የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከባንካችን ጋር ለሚሰሩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ያልተቆጠብ ድጋፍ ለማድረግ ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት በመምጣቱ ደስተኛ መሆናቸውን የተናገሩት የቶፕ ቢቬሬጅ እና ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ መስራችና ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ድንቁ ከባንኩ ጋር በመስራታቸው ይበልጥ ውጤታማ እንዳደረጋቸው ገልፀዋል።

ዛሬ በተካሄደው የጉብኝት እና የውይይት መርሃ ግብር ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ቶፕ ቢቬሬጅ እና ኢንዱስትሪ ትሬዲንግ ከዚህ በፊት አብረው ሲሰሩ ይስተዋሉ የነበሩ ጠንካራ ጎኖች እንዲሁም ሊስተካከሉ ይገባል በተባሉ የአሰራር ስርዓት ዙሪያ ጥልቅ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይም በጋራ መስራት በሚቻልበት አስቻይ ሁኔታዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ከተሞች እያካሄደው የሚገኘው የውይይት መድረክ ደንበኞች በአገልግሎት አሰጣጥ እና በባንክ አገልግሎት ዙሪያ ለሚያነሷቸው ሀሳብ እና አስተያየቶች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ታሳቢ በማድረግ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና አርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 14 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 13 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ...