ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከጅማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጋር በጋራ መስራት በሚቻልበት ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት አደረገ።

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና የጅማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በተለያዩ ዘርፎች በጋራ መስራት በሚቻልበት ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ የሁለቱም ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት መጋቢት 06 ቀን 2018 ዓ.ም በመጅሊሱ ዋና ጽ/ቤት ተወያይተዋል።

በውይይቱ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታውች ላይ ያጠነጠነ ሲሆን በተለይ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፍ እና ተደራሽ በሚሆንበት ዙሪያ በጥልቀት ውይይት አድርገዋል።

በጅማ ከተማ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚው ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት የጅማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ኃላፊ ሼህ መሐመድ አሚን ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ አዳዲስ ቅርንጫፎችን እንዲከፍት ጠይቀዋል።

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን በበኩላቸው ባንካችን በሁሉም ቅርንጫፍ መስኮቶች ከሚሰጠው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልፀው በጅማ ከተማም አስፈላጊው ጥናት ተደርጎ ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በመክፈት ቀልጣፋ እና የከተማውን ህዝብ የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሁሉም የሀይማኖት ተቋማት ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል የተለያዩ ስራዎች እየተከወኑ መሆኑን የባንኩ ኃላፊዎች ገልፀዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና አርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 14 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 13 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ...