ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ ለደንበኞቹ የኢፍጣር ፕሮግራም አዘጋጀ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የመተሳሰብ ተምሳሌት የሆነውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ በድሬዳዋ ከተማ ለሚገኙ ደንበኞች የኢፍጣር መርሃ-ግብር መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል።

በዝግጅቱ ላይ የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ በድሬዳዋ ከተማ የሚገኙ ደንበኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የከተማዋ መጅሊስ ተወካዮች ታድመዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከንግድ እንቅስቃሴው ባሻገር ማህበራዊና ሃይማኖታዊ እሴቶችን ማክበርና ከደንበኞቹ ጋር ያለውን መልካም ትስስር ይበልጥ እንዲጠነክር ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከወኑ መሆኑን የማርኬቲንግና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ በመርሃ ግብሩ ወቅት ባደረጉት ንግግር አመላክተዋል።

የዛሬውን ጨምሮ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ያካሄድነው የኢፍጣር ፕሮግራም ከደንበኞቻችን ጋር ያለንን ቤተሰባዊ ትስስር የምናድስበትና ለሰጡን እምነት ምስጋና የምናቀርብበት ነው ያሉት አቶ ቢኒያም፤ ባንካችን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን (ግሎባል ሐቂቃ) ተደራሽነት ይበልጥ ለማስፋት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ረመዳን የሰላም፣ የፍቅርና የልግስና ወር መሆኑን የጠቀሱት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መጅሊስ ተወካይ እና የመስጅዶችና አቁዋፍ ኃላፊ ሼህ አብደላ አሜ፤ ለተደረገው ኢፍጣር ምስጋናቸውን አቅርበው ተቋማት ማህበረሰቡን በሚጠቅሙ ተግባራት ላይ መሰማራታቸው በህዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት እንደሚያጠናክር በአፅንኦት ተናግረዋል።

በኢፍጣር ፕሮግራሙ ላይ የታደሙ የባንኩ ደንበኞች፣ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ የሰጠውን ክብርና ያሳየውን መልካም ግንኙነት አድንቀዋል።

በከተማዋ ለሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎችና ግለሰቦች ምቹ የሆኑ የባንክ አገልግሎቶችን እያቀረበ እንደሚገኝ የጠቀሱት በኢፍጣር መርሃ ግብሩ የታደሙ ደንበኞች ይኸን መሰል ዝግጅት በባንኩና በደንበኛው መካከል ያለውን ግልፅነትና መተማመን ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች 1447ኛውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ በኢኮኖሚ ዝቅ ላሉ ሰዎች የተለያዩ የአስቤዛ ድጋፎችንና ለደንበኞች ደግሞ በጋራ የሚያፈጥሩበትን መድረክ እያዘጋጀ ይገኛል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና አርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 14 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 13 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ...