በላቀ አመራር ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በላቀ የአመራር ሰጭነት Advanced Leadership Training ዙሪያ ለባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት በስካይ ላይት ሆቴል ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም አጠናቋል፡፡

ስልጠናው ከአልቲሜት የማማከር አገልግሎት ጋር በመተባበር የተሰጠ ሲሆን የባንኩን ሁለንተናዊ የአመራር አቅም ይበልጥ ለማጠናከር፣ የውሳኔ አሰጣጥ ጥራትን ለማሻሻል እና በተለዋዋጭ የባንክና የፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ በተቀመጡ መለኪያዎች ሁሉ የላቀ አመራር የሚሰጡ መሪዎች እንዲኖሩ ማስቻል የስልጠናው ዓላማ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ዘመኑን የዋጀ አመራር ባህሪያት፣ ስትራቴጂካዊ አመራር፣ የቡድን መሪነት እና የተግባቦት ክህሎት፣ እንዲሁም ውጤት ተኮር አመራር ስልጠናው ትኩረት አድርጎ ካጠነጠነባቸው ርዕሶች መካከል ናቸው፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለሰራተኞቹ እና ለከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተለያዩ የአጭር እና የረዥም ጊዜ ስልጠናዎችን በማሰናዳት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የዛሬው ስልጠና የባንኩን ተቋማዊ የአመራር አቅምን በማጠናከር የተጀመረውን የስኬት ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠል አይነተኛ ሚና ይጫወታል ተብሏል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና አርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 14 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 13 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ...