ግሎባል ቱር በሽረ እንደስላሴ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሄደ።

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና አጠቃላይ የባንኩን ነባራዊ ሁኔታ ለደንበኞቹ የሚያስተዋውቅበት “ግሎባል ቱር” የተሰኘውን መርሃግብር በሽረ እንደስላሴ ከተማ በሚገኘው ቅርንጫፍ በተለያዩ ዝግጅቶች ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በድምቀት አካሂዷል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ስሙን የሚመጥን አገልግሎት በመላው የሀገራችን ክፍል እየሰጠ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ወቅት ባደረጉት ንግግር የገለፁት የኮርፖሬት ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሳህለሚካኤል መኮንን አዳዲስ የቴክኖሎጅ ግኝቶችን በማካተት ለደንበኞች ምቹ፣ ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት በሙሉ አቅም እየሰራን ነው ብለዋል።

በሽረ የተከፈተው ቅርንጫፍ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ተመራጭ የሆነ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን በአፅንኦት የገለፁት ቺፍ ኦፊሰሩ የሚስተካከሉ ክፍተቶች ካሉም በፍጥነት ለማረም ዝግጁ ነን ብለዋል።

የባንኩን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል የመወያያ ርዕስ ያቀረቡት ደግሞ የደንበኞች ግንኙነት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ መሠረት አሰፍ ናቸው።

በቀረበው የመወያያ ርዕስ አስመልክቶ ከንግዱ ማህበረሰብ ለተነሱ አስተያየት እና ጥያቄዎች በባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የሽረ እንደስላሴ ከተማ ንግድ ም/ቤት ፕሬዘዳንት መምህር ፍስሃ ገብሩ በበኩላቸው ከተማዋ ከፍተኛ የንግድ ማዕከል መሆኗን ገልፀው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያም የንግድ ማህበረሰቡን በሙሉ አቅም ለማገልገል ወደ ከተማችን ስለመጣችሁ በም/ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ወደፊትም ከባንኩ ጋር  አብረን ልንሰራባቸው በሚቻል ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት ለማድረግ ቢሮው ዝግጁ መሆኑን ፕሬዘዳንቱ ገልፀዋል።

በግሎባል ቱር  የተሳተፉ የንግዱ የማህበረሰብ ክፍሎች በበኩላቸው ከባንኩ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የኮርፖሬት ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሳህለሚካኤል መኮነን፣ የማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ፣ የደንበኞች ግንኙነት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ መሠረት አሰፍ፣ የምዕራብ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሠለሞን ግርማ፣ የሽረእንደስላሴ ከተማ ንግድ ም/ቤት መምህር ፍስሃ ገብሩ እንዲሁም የንግዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ግሎባል ቱር በቀጣይም በተለያዩ ከተሞች እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር ዋነኛ መርህ አድርጎ እየሰራ ነው – ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማጠናከር ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት ዋና ዕሴት አድርጎ እየሰራ መሆኑን...

ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ዉጤት መመዝገቡ ተገለፀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በበርካታ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ የቦርድ አመራር እና የማኔጅመንት አባላት ገለጹ፡፡...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተሳተፈበት ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ነህሚያ የኦቲዝም ማዕከል የ2018 ዓ.ም የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብርን ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች አከናውኗል።...