
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ የስኬት መዳረሻ ብርቱ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል የባንኩ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን ገለፁ።
አቶ ሳኅለሚካኤል ይኸን ያሉት ሮዜታ ሪል እስቴት ከግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተደረገለት የፋይናንስ ድጋፍ የንግድ ሱቆቹን እና አፓርትመንቶችን በድሬዳዋ ከተማ ገንብቶ ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ለሽያጭ ባቀረበበት ወቅት ነው።
የተገነቡት የንግድ ሱቆች ዘመናዊ ዲዛይንና ለንግድ ሥራ ምቹ መሆናቸውን የገለፁት የሮዜታ ሪል እስቴት መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው ፕሮጀክቱ በድሬዳዋ ከተማ የንግድ እንቅስቃሴን ለማጠናከር አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ያደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ፕሮጀክቱ በጊዜው እና ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ማስቻሉንም አቶ ቴወድሮስ አመላክተዋል።
ባንኩ ለሪል እስቴትና ለንግድ ዘርፍ የሚያገለግሉ ፕሮጀክቶችን በመደገፍ የከተሞችን የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ውስጥ የራሱን አሻራ እያስቀመጠ መሆኑን የገለፁት የኮርፖሬት ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን ፤ ደንበኞች የፋይናንስ አገልግሎት እንዲያገኙ የተለያዩ የብድር አማራጮችን አቅርቦ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።



ደንበኞቹ የሚያልሙትን ዓላማ እውን በማድረግ ለስኬታቸው መዳረሻ ብርቱ አጋር መሆን የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዕሴት መሆኑን ያወሱት አቶ ሳኅለሚካኤል በቀጣይም ደንበኞቻችን በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሁኑ ያልተቆጠበ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።
የባንካችን ደንበኞች የንግድ ቤት እና የመኖሪያ አፓርትመንት ከሮዜታ ሪል እስቴት ሲገዙ ከ80% በላይ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ብድር እንደሚያመቻች ተገልጿል።
በመርሀ ግብሩ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች፣ የነጋዴ ማህበረሰብ አባላት፣ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና የሮዜታ ሪል እስቴት አመራሮች ተገኝተዋል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!