ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በቀርጫንሼ ግሩፕ የጉብኝት መርሃ ግብር አካሄደ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ግሎባል ቱር” በሚል መሪቃል የሚያካሂደውን የደንበኞችን የስራ እንቅስቃሴ የመጎብኘት እና የውይይት መርሃ ግብር ታኅሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በቀርጫንሼ ግሩፕ አካሂዷል።

በጉብኝት መርሃ ግብሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው፣ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ፣ የቦርድ አባላት፣ ቺፍ ኦፊሰሮች እና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ቀርጫንሼ ግሩፕ አብረው ሲሰሩ መቆየታቸውን ያወሱት የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ኃላፊወች አብረው መስራት የሚችሉበትን መንገድ አጠናክሮ ማስቀጠል የጉብኝት መርሃ ግብሩ ዋና አላማ መሆኑን ተናግረዋል።

የባንኩ ቦርዶች እና የስራ ኃላፊዎች የቀርጫንሼን ግሩፖ የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከትና በቀጣይ አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ለመወያየት በመምጣታቸው አድናቆታቸውን የገለፁት የግሩፑ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር እስራኤል ደግፌ፤ ግሩፓቸው ውጤታማ እንዲሆን ከባንኩ ጋር በጋራ መስራቱ አበርክቶው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

ግሩፑ በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው በዋነኝነት በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አስመጭና ላኪ፣ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ እንዲሁም በሆቴል አገልግሎት ዙሪያ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

ቀርጫንሼ ግሩፕ በተለያዩ ግዙፍ በሆኑ ሀገርንና ህዝብን በሚጠቅሙ ፕሮጄክቶች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ መመልከታቸውን የገለፁት የባንኩ የስራ ኃላፊዎች ግሩፑን በፋይናንስ እና በሀሳብ ለመደገፍ ለሁለንተናዊ ዕድገት እና ለጋራ ስኬት የተለመደውን ያልተቆጠበ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ደንበኛ ብቻ ሳይሆን ባለድርሻ አካላት ጭምር መሆናቸውን የተናገሩት የቀርጫንሼ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ከባንኩ ጋር ለመስራት ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ቀርጫንሼ ግሩፕ  ለበርካታ ዓመታት በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸው በውይይቱ ወቅት የተነገረ ሲሆን በስራ ወቅት ያጋጠሙ እንከኖችን በመቅረፍ እና የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ለጋራ ስኬት በጋራ ለመስራት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል የደንበኞችንና የባለድርሻ አካላትን የስራ እንቅስቃሴ የመጎብኘት እና አብሮ መስራት የሚቻልበትን አስቻይ ሁኔታ የመፍጠር መርሃ ግብር ወደፊትም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ

ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በእንጦጦ ተራራ...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2025/26 የሥራ አፈጻጸምን ገምግሞ ለ2026/27 ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የ2025/26 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም የገመገመበትን መርሃ ግብር ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር ዋነኛ መርህ አድርጎ እየሰራ ነው – ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማጠናከር ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት ዋና ዕሴት አድርጎ እየሰራ መሆኑን...