ዲጂታል የኢንሹራንስ እና የአረቦን ብድር አገልግሎት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከኒያላ ኢንሹራንስ እና ከካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ጋር በመተባበር ዲጂታል የኢንሹራንስ እና የአረቦን ብድር አገልግሎትን ሀምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ አስጀምሯል፡፡

በመርሃ ግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዲጂታል ባንኪንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ መቅደስ በቀለ፣ የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ቺፍ ከስተመር ማኔጅመንት ኦፊሰር አቶ ተገኝ ማስረሻ፣ የካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሀም ጥላሁን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የተለመደው የኢንሹራንስ አገልግሎት ደንበኞች ቅርንጫፍ ቢሮ ድረስ በአካል ሄደው የሚያገኙት የነበረ ሲሆን ዲጂታል የኢንሹራንስ እና የአረቦን ብድር አገልግሎት በማንኛውም ሰአት እና ቦታ ሆነው ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም የኢንሹራንስ ሽፋን ማግኘት መቻላቸው ጊዜን ከመቆጠብ አልፎ በሀገራችን የሚታየውን የኢንሹራስ ተደራሽነት ችግር በሰፊው ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በስምምነቱ መሰረት የኒያላ ኢንሹራንስ ደንበኞች ወደ ኢንሹራንስ ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ቦታ ሆነው ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ለንብረታቸው የመድን ሽፋን ዋስትና መግዛት የሚችሉበት ሙሉ በሙሉ ዲጂታል የሆነ አገልግሎት ሲያስጀምር፤ ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ የቴክኖሎጂ እና የዲጂታል መተግበሪያ የማቅረብ ድርሻ ሲኖረው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የአረቦን ክፍያቸውን ተበድረው መክፈል ለሚፈልጉ ደንበኞች የብድሩን ገንዘብ አቅርቦት ተደራሽ ያደርጋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከሉሲ ኢንሹራንስ ጋር ተመሳሳይ አገልግሎት ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና አርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከአርፋሳ ጀኔራል ትሬዲንግ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 14 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራት ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ማጠናከር የሚያስችል ውይይት መስከረም 13 ቀን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ...