የሁለት ሚሊዬን ብር ድጋፍ ተደረገ !!!

Share the Post:

የሁለት ሚሊዬን ብር ድጋፍ ተደረገ !!!

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ብር ሁለት ሚሊዬን በማዕከሉ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድጋፍ እና ጉብኝት አድርጓል፡፡

“ለህብረተሰቡ መስጠት” የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አንዱ ዕሴት መሆኑን ድጋፉን ባበረከቱበት ወቅት ያወሱት የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳህለሚካኤል መኮንን የዛሬው ድጋፍም ባንካችን ለወገኖቹ ብርቱ አጋር መሆኑን ያሳየበት የድጋፍ መርሃ ግብር ነው ብለዋል ፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ድጋፍ ሲያደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም የመጨረሻውም አይሆንም ያሉት አቶ ሳኅለሚካኤል በቀጣይም ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተቋማት እና የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ተናግረዋል ፡፡

የመቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል መስራች ክቡር ዶክተር ብንያም በለጠ በበኩላቸው ባንኩ ላደረገው ድጋፍ በአረጋውያንና በተረጂዎች ስም ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን

Related Posts

የሁለት ሚሊዬን ብር ድጋፍ ተደረገ !!!

የሁለት ሚሊዬን ብር ድጋፍ ተደረገ !!! ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ብር ሁለት ሚሊዬን በማዕከሉ...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን በተከሰተው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች 1 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ብር ድጋፍ አደረገ

ባንካችን በቅርቡ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖቻችንን ቦታው ድረስ በመገኘት...