
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በ2024/25 የሒሳብ ዓመት ባንኩ ባስቀመጠው የመለኪያ መስፈርት መሠረት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል።
በተቀመጠው የመለኪያ መስፈርት መሠረት ከምስራቅ አዲስ አበባ፣ ከምዕራብ አዲስ አበባ እንዲሁም ከደቡባዊ ዲስትሪክት እስከ ሶስት ለወጡ ቅርንጫፎች በባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል።
አትላስ፣ አዳማፓንአፍሪክ እና ገላን ኮንደሚኒየም ከምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፤ ኮተቤ፣ፖፑላሬ እና ቀበና ቅርንጫፎች ከምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት እንዲሁም ሚዛን፣ ቡሌሆራ እና ዲላ ቅርንጫፍ ከደቡባዊ ዲስትሪክት ተሸላሚ ሆነዋል።
ክብሩ ፍቃዱ፣ራሄል በቀለ እና ትዕግስት ቦጋለ ደግሞ ከደንበኞች ግንኙነት መምሪያ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እውቅና ሲሰጣቸው፤ ተስፋዬ ገ/መድህን፣ እሱባለው አለምነው እና ኤፍሬም አስፈው አጠቃላይ ካሉ ቅርንጫፎች መካከል ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።



ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተሻለ አፈፃፀም ለሚፈፅሙ ቅርንጫፎች እና ሠራተኞችን ማበረታታት አንዱ ዕሴት መሆኑን በሽልማት መርሃ ግብሩ ወቅት የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው ዶ.ር ተስፋዬ ቦሩ በተያዘው የሂሳብ ዓመትም ተሸላሚዎች ይበልጥ እንዲበረቱ እና ሌሎቹ በቀጣይ ተሸላሚ እንዲሆኑ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ሽልማቱን የተረከቡ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች በበኩላቸው ሽልማቱ ይበልጥ እንዲሰሩ እንደሚያነሳሳቸው አውስተው ውጤቱ የመጠው አጠቃላይ ከቅርንጫፍ ሰራተኞች ጋር በመሆኑ በቀጣይም ይኸንኑ ስኬት ለማስቀጠል ቁርጠኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዛሬው መርሃ ግብር ከ15 በላይ ቅርንጫፎች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷችዋል።