ባንካችን በጅማ ከተማ ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ 1447ኛውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ በጅማ ከተማ ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ አካላት ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በቡካሪ መስጂድ  አከናውኗል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት የባንኩ ዋነኛ እሴት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት የባንካችን ኮርፖሬት ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን ዛሬ ያካሄድነው ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ይኸንኑ ዕሴት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

ዛሬ የተደረገው ድጋፍ የረመዳን ወር የሚያስተምረውን የመረዳዳት እና የመተጋገዝ እሴት መሠረት በማድረግ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ወቅት የገለፁት አቶ ሳኅለሚካል፤ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች የጾም ወራቸውን ያለስጋት እንዲያሳልፉ ያስችላል ብለዋል።

የጅማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ኃላፊ ሼህ መሐመድ አሚን በበኩላቸው ባንኩ በረመዳን ወር ላሳየው አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበው የሚደረገው ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ከህዝቡ ጎን መሆኑን በተግባር እንደሚያረጋግጥ ያመላከቱት ደግሞ የማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ ናቸው።

ዛሬ በተከናወነው ማዕድ ማጋራት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 80 ሰዎች የተለያየ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

በማዕድ ማጋራት መርሃ ግብሩ የባንካችን ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን፣ የባንካችን ከፍተኛ የሼሪዓ አማካሪ ሼህ ሚስባህ አብዱራህማን ፣ የጅማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ኃላፊ ሼህ መሐመድ አሚን፣ የማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ፣ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዳይሬክተር ሱሌማን አብደላ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ከባለአክሲዮኖች ጋር የሚደረገው የውይይት መድረክ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከባለአክሲዮኖቹ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችለውን የውይይት መድረክ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም...

ባንኩ የተቋቋመበትን ዓላማ እንዲያሳካ ያልተቆጠበ ድጋፍ እናደርጋለን – ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ባንኩ የተጣለበትን ሀገራዊ እና ማህበራዊ ኃላፊነት በተሟላ ሁኔታ ተወጥቶ የተቋቋመበትን ዓላማ እውን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በእንጦጦ ተራራ...