
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቅዱስ የሆነውን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰርለና በጎ አድራጎት ድርጅት የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡
ባንካችን ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን ይኸን መሰል የበጎ አድራጎት ተግባራትን ለረዥም ጊዜ እያከናወነ እንደሚገኝ የገለጹት የማርኬቲንግና እና ኮምዩኒኬሽስ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ በተለያዩ ጊዜ ባንኩ የሚያደርጋቸው ድጋፎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል፡፡
የረመዳን ወር የመረዳዳትና የመተሳሰብ ወር መሆኑን ያወሱት አቶ ቢኒያም ባንካችን የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት እና የኢፍጣር መርሃ ግብር በማሰናዳት ለጋራ ስኬታችን የሚለውን መሪ ቃል በተግባር ያረጋገጠበት መሆኑንም አክለዋል፡፡
የሲርለና በጎ አድራጎት ድርጅት የተቸገሩ ዜጎችን በመደገፍ፣ ወላጅ አልባ የሆኑ ህፃናትን በቋሚነት በመርዳት እና የተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ እንደሚገኝ የገለጹት የሲርለና በጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የምንሰራውን በጎ ተግባር በሁለንተናዊ መልኩ ለመደገፍ እና የዛሬውነ ኢፍጣር ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በማዘጋጀቱ በተቸገሩ ወገኖች ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡




ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆዎችንና አሠራሮችን የተከተለ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በባንካችን ሁሉም ቅርንጫፍ መስኮቶች እና ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ ቅርንጫፎቻችን አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝ የገለጹት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሱሌማን አብደላ ባንካችን ለሚሰጠው የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ረመዳን የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የአንድነት ወር መሆኑን የገለጹት አቶ ሱሌማን በዚህ በተቀደሰ ወር ከወገኖቻችን ጋር ማዕድ በመካፈላችን እንደባንክ ትልቅ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል፡፡
በኢፍጣር መርሃ ግብሩ ላይ የታደሙትና በድርጅቱ ድጋፍ የሚደረግላቸው ግለሰቦች በበኩላቸው ባንኩ ያደረገው ኢፍጣር እንደተረሳን እንዳይሰማን አድርጎናል ብለዋል፡፡
በዕለቱ የሰርለና በጎ አድራጎት ድርጅት የስራ እንቅስቀሴ የባንካችን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ተዟዝረው የጎበኙ ሲሆን ድርጅቱ እየሰራው ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ላደረገው የኢፍጣር መርሃ ግብር ከድርጅቱ የዕውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቶታል፡፡
በኢፍጣር መርሃ ግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ከፍተኛ የሸሪዓ አማካሪ ሼህ ሚስባህ አብዱራህማን፣ የማርኬቲንግና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ፣ ከወለደነፃ የባንክ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሱሌማን አብደላ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ሲሆን በቀጣይም ድጋፍ ለሚሹ የተለያዩ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ግሎባል በንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!