ለአዲሱ የቦርድ ሥራ አመራር አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር ተካሄደ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዲስ ለተመረጡ የቦርድ ሥራ አመራር አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ እና ሥራ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ሰኔ 09 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት አካሂዷል፡፡

ባንኩ ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በማረም እና ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል በማይናወጥ የእድገት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የገለጹት የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ፤ አዲሶቹ የቦርድ አባላት ከባንኩ የማኔጅመንት አባላት ጋረ በመቀናጀት የባንኩን ራዕይ እውን ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ባንኩን ላለፉት ዓመታት በብቃት በማገልገል እዚህ ደረጃ ላደረሱት የቀድሞ የቦርድ አመራር አባላት ዶ/ር ተስፋዬ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አዲሶቹ የቦርድ ሥራ አመራር አባላት አቶ ዮሴፍ ጌታቸውን በቦርድ ሰብሳቢነት እንዲሁም ዶ/ር ዮናስ ሀጎስን ምክትል ሰብሳቢ በማድረግ መርጧል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለአዲሶቹ የቦርድ አባላት መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኛል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር ዋነኛ መርህ አድርጎ እየሰራ ነው – ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማጠናከር ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት ዋና ዕሴት አድርጎ እየሰራ መሆኑን...

ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ዉጤት መመዝገቡ ተገለፀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በበርካታ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ የቦርድ አመራር እና የማኔጅመንት አባላት ገለጹ፡፡...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተሳተፈበት ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ነህሚያ የኦቲዝም ማዕከል የ2018 ዓ.ም የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብርን ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች አከናውኗል።...