በተሰለፈበት ሁሉ ማሸነፍ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ መለያ እንዲሆን እየተሰራ ነው – ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተሰማራበት የሥራ ዘርፍ ሁሉ ቀዳሚ እና አሸናፊ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ተናገሩ፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ ይኸን ያሉት ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ምርጥ የቁጠባ ባንክ ዘርፍ ተሸላሚ መሆኑንና የባንኩ የእግር ኳስ ቡድን የ2017 ዓ.ም የባንኮች እግር ኳስ ውድድርን በበላይነት ማጠናቀቁን አስመልክቶ ዋንጫውን ለዋና ሥራ አስፈፃሚው ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በአስረከበበት ወቅት ነው፡፡

ስፖርት ለአእምሮ ጤናና ለአካል ብቃት ግንባታ አይተኬ ሚና እንደሚጫወት የገለጹት ዶ/ር ተስፋዬ ሠራተኞቻችን ንቁ በመሆንና ጤናቸውን በመጠበቅ በቋሚ ስራቸውም አይበገሬ እና አሸናፊ በመሆን የባንኩን ራዕይ እውን ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ባንኩ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ኢንዱስትሪው የሚፈልጋቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ለደንበኞቻችን ምቹ እና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት በመስጠት በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ እውቅናዎችን እያገኘ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ተስፋዬ ወደፊትም በደንበኞች ዘንድ ተመራጭ የባንክ አገልግሎት ከሚሰጡ ባንኮች መካከል ግንባር ቀደም ለመሆን ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የእግር ኳስ ቡድኑ ላስመዘገበው ውጤት ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ወደፊትም ቡድኑን በሁለንተናዊ መልኩ ለመደገፍ እና ለማበረታታት እንደማይቆጠቡ ተናግረዋል፡፡

የ2017 ዓ.ም የባንኮችን እግር ኳስ ውድድርን ላሸነፈው የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን አባላት የተለያዩ የማበረታቻ ሽልማቶች ተደርጎለታል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ከባለአክሲዮኖች ጋር የሚደረገው የውይይት መድረክ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከባለአክሲዮኖቹ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችለውን የውይይት መድረክ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም...

ባንኩ የተቋቋመበትን ዓላማ እንዲያሳካ ያልተቆጠበ ድጋፍ እናደርጋለን – ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ባንኩ የተጣለበትን ሀገራዊ እና ማህበራዊ ኃላፊነት በተሟላ ሁኔታ ተወጥቶ የተቋቋመበትን ዓላማ እውን...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አመራሮችና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በእንጦጦ ተራራ...