ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ምርጥ የቁጠባ ባንክ ዘርፍ አሸናፊ ሆነ

Share the Post:

የአፍሪካ የባንክ እና ኢንሹራንስ ሽልማት በታንዛኒያ ዋና ከተማ ዳሬሰላም በተለያዩ ዘርፎች የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ባንኮች እና ኢንሹራንሶች የሽማልት ሥነ ስርዓት ሰኔ 06 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በአፍሪካ የባንክ እና ኢንሹራንስ ሽልማት ላይ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ምርጥ የቁጠባ ባንክ ዘርፍ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ተመራማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዘመኑ የደረሰበት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለደንበኞች ምቹ፣ቀላል፣ፈጣን እና አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ በሽልማት ሥነ ስርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር የገለጹት የማርኬቲንግና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ ባንኩ ሽልማቱን እንዲያሸንፍ ድርሻቸውን ለተወጡ የባንኩ ሠራተኞች፣ አመራሮች እና ደንበኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ እንዲሁም በመላው ዓለም አወንታዊ ተፅዕኖ በማድረግ ተደራሽ እና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሆነም በሽማልቱ ወቅት ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ግሎባ ባንክ ኢትዮጵያ በ2016 ዓ.ም በአቢሲንያ የኢንደስትሪ ሽልማት ድርጅት በባንኮች ዘርፍ የወርቅ ደረጃ የኢንደስትሪ ሽልማት አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ግሎባል ባንከ ኢትዮጵያ

ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር ዋነኛ መርህ አድርጎ እየሰራ ነው – ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማጠናከር ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት ዋና ዕሴት አድርጎ እየሰራ መሆኑን...

ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ዉጤት መመዝገቡ ተገለፀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በበርካታ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ የቦርድ አመራር እና የማኔጅመንት አባላት ገለጹ፡፡...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተሳተፈበት ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ነህሚያ የኦቲዝም ማዕከል የ2018 ዓ.ም የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብርን ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች አከናውኗል።...