
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ግሎባል ቱር” በተሰኘ መሪ ቃል እያካሄደ የሚገኘውን የባንኩን ከፍተኛ ደንበኞች እና ባለድርሻ አካላት የመጎብኘት መርሃ ግብር አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።
ግሎባል ቱር በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ሲሆን ጥር 09 ቀን 2018 ዓ.ም በሆራ ኮርፖሬት ግሩፕ የመስክ ምልከታ ተደርጓል።
የባንኩ ኃላፊዎችና የቦርድ አባላት የኮርፖሬት ግሩፑን ሁለንተናዊ የስራ እንቅስቃሴ በመስክ ምልከታ በመጎብኘታቸው ምስጋናቸውን ያቀረቡት የሆራ ኮርፖሬት ግሩፕ ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አደም ከድር ፤ የመስክ ምልከታው ከድርጅታችን ጋር ለበርካታ ዓመታት በጋራ ስንሰራ የነበረውን አሰራር የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆናችሁን ያንፀባርቃል ብለዋል።
ድርጅቱ በበርካታ የስራ ዘርፎች በተለይም በአስመጭ እና ላኪነት፣ በሪል እስቴት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በአውቶሞቲቭ እና በማኑፋክቸሪንግ የስራ ዘርፎች ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ እንደሚገኝ አቶ አደም ገልፀዋል።





ሆራ ኮርፖሬት ግሩፕ በበርካታ የስራ ዘርፎች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ መመልከታቸውን የገለፁት የባንኩ ኃላፊዎች በበኩላቸው ግሩፑ የሀገራችንን ኢኮኖሚ ዕድገት በተግባር እየደገፈ መሆኑን አመላክተው ከሆራ ኮርፖሬት ግሩፕ እና መሠል ተቋማት ጋር መስራት የባንኩ የስትራቴጂ አቅጣጫ አንዱ አካል መሆኑን ገልፀዋል።
በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ እና በሆራ ኮርፖሬት መካከል ያለው የረጅም ዘመን የስራ ግንኙነት በሁለቱም ድርጅቶች እድገት ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ በመርሃ ግብሩ ወቅት ተነግሯል።
የመስክ ምልከታ መርሃ ግብሩ የነበረውን የስራ ትብብር ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሻገር ወደፊትም ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በመስክ ምልከታ መርሃግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ ጌታቸው፣ የቦርድ አባላት፣ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ፣ ቺፍ ኦፊሰሮች እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ግሎባል ቱር በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው ከፍተኛ ደንበኞችንና ባለድርሻ አካላትን የመጎብኘት መርሃ ግብር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!