ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በጅማ ከተማ ለሚገኙ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ

Share the Post:

1447ኛውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም  በለይሌ ሪዞርት በተሰናደው የኢፍጣር መርሃ ግብር የባንካችን ኃላፊዎች፣ ደንበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የደንበኞችን ፍላጎት ማዕከል ያደረግ ምቹ እና ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ወቅት የገለፁት ቺፍ ኮርፖሬት ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ ሳኅለሚካኤል መኮንን በቀጣይም የደንበኞቻችንን ፍላጎት የሚያሟላ አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆንን አመላክተዋል።

በኢፍጣር መርሃ ግብሩ ተሳታፊ የሆኑ የባንካችን ከወለድ ነፃ ደንበኞች በበኩላቸው ባንኩ ለአዘጋጀው ኢፍጣር ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም ከባንኩ ጋር ያላቸውን የስራ ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።

1447ኛውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ ባንካችን በተለያዩ ከተሞች ማዕድ የማጋራት እና የኢፍጣር መርሃ ግብር እያከናወነ ይገኛል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር ዋነኛ መርህ አድርጎ እየሰራ ነው – ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በማጠናከር ለጋራ ስኬት በጋራ መስራት ዋና ዕሴት አድርጎ እየሰራ መሆኑን...

ባለፉት ዘጠኝ ወራት አመርቂ ዉጤት መመዝገቡ ተገለፀ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በበርካታ መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ የቦርድ አመራር እና የማኔጅመንት አባላት ገለጹ፡፡...

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተሳተፈበት ዓለም አቀፍ የኦቲዝም ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ነህሚያ የኦቲዝም ማዕከል የ2018 ዓ.ም የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብርን ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች አከናውኗል።...