
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ዙር የአርንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አቢሲኒያ ውሃ ፋብሪካ አካባቢ ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም አካሄዷል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
የዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ይገኛል፡፡



ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሃ ግብር ያካሄደ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከ5 ሺህ በላይ ችግኞች ተተክለዋል።
ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በተለያዩ ሁነቶች እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን አረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሃ ግብር ማህበራዋ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው ተግባራት መካከል አንዱ ነው።
ዛሬ የተተከሉት ችግኞች በቀጣይ አመታት የተለያዩ ፍራፍሬዎችን የሚሰጡ መሆናቸውን የተናገሩት በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የተሳተፉ ሰራተኞች ችግኞቹ እንዲፀድቁ ያልተቆጠበ ክትትል እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!