በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት አመርቂ ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ

Share the Post:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ባንኩ ባስቀመጣቸው መለኪያዎች መሰረት የሚበረታታ ውጤት ማስመዝገቡን የባንኩ የቦርድ እና የማኔጅመንት ዓባላት ገለፁ፡፡

የባንኩ የቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት ያለፉት ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀምን ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ገምግመዋል፡፡

የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ፣ የብድር አቅርቦት፣ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ማስፋፋት፣ የደንበኞች እርካታን ማሻሻል እና ትርፋማነትን በማጠናከር ዙሪያ ባለፉት ስድስት ወራት የሰራው ስራ ከዕቅድ በላይ እንደሆነ በግምገማው ወቀት ተነግሯል፡፡

በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት በተቀመጡ የአፈጻጸም መለኪያዎች መሰረት ከዕቅድ በላይ ውጤት እንድናስመዘግብ የላቀ አመራር በሚሰጡ የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና በሰራተኞቻችን ቁርጠኝነት የመጣ ውጤት መሆኑን የገለፁት የቦርድ አባላት በሁለተኛው መንፈቅ ዓመትም ከዕቅድ በላይ ውጤት ለማስመዝገብ የተለመደው ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ባንኩ በቀጣይ መንፈቅ ዓመት የዲጂታል አገልግሎቶቹን ለማስፋት፣ የደንበኞች እርካታን ለማሻሻል እና የሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገትን ለመደገፍ ለተለያዩ ደንበኞች የሚያቀርበውን ፋይናንስ አጠናክሮ ማስቀጠል በቀጣይ ስድስት ወራት በልዩ ትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

Related Posts

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሪሞን ጀነራል ትሬዲንግን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ተ/ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሳኅለሚካኤል መኮንን የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ፣ የሪሞን ጀነራል ትሬዲንግን የሥራ...

ከባለአክሲዮኖች ጋር የሚደረገው የውይይት መድረክ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከባለአክሲዮኖቹ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችለውን የውይይት መድረክ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም...

ባንኩ የተቋቋመበትን ዓላማ እንዲያሳካ ያልተቆጠበ ድጋፍ እናደርጋለን – ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ባንኩ የተጣለበትን ሀገራዊ እና ማህበራዊ ኃላፊነት በተሟላ ሁኔታ ተወጥቶ የተቋቋመበትን ዓላማ እውን...