
በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ተ/ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሳኅለሚካኤል መኮንን የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ፣ የሪሞን ጀነራል ትሬዲንግን የሥራ እንቅስቃሴ የጉብኝት እና የውይይት መርሃ ግብር መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ ባንካችን ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር፣ የድርጅቱን ሁለገብ የሥራ እንቅስቃሴ በቅርበት መመልከት እና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ መሆኑን ዶ/ር ሳኅለሚካኤል መኮንን በውይይቱ ወቅት ገልጸዋል።



ሪሞን ጀነራል ትሬዲንግ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በተለያዩ የልማት ዘርፎች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ የገለጹት የድርጅቱ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አያሌው፤ ከግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን መልካም የሥራ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን መልካም የስራ ግንኙነት በዘላቂነት ለማስቀጠል እና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለመፍጠር የሚያስችሉ የጉብኝት እና የውይይት መርሃ ግብሮችን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን